መዝሙር
በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር። ማህሌት።
92 ለይሖዋ ምስጋና ማቅረብ ጥሩ ነው፤+
ልዑሉ አምላክ ሆይ፣ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር መዘመር መልካም ነው፤
2 ታማኝ ፍቅርህን በማለዳ፣
ታማኝነትህንም በሌሊት ማሳወቅ+ መልካም ነው፤
3 አሥር አውታር ባለው መሣሪያና በክራር፣
ደስ በሚል የበገና ድምፅ+ ታጅቦ ማሳወቅ ጥሩ ነው።
4 ይሖዋ ሆይ፣ ባከናወንካቸው ነገሮች እንድደሰት አድርገኸኛልና፤
ከእጅህ ሥራዎች የተነሳ እልል እላለሁ።
5 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ታላቅ ነው!+
ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!+
6 ማመዛዘን የጎደለው ሰው ይህን ሊያውቅ አይችልም፤
ሞኝ የሆነም ሰው ይህን ሊረዳ አይችልም፦+
8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ከሁሉ በላይ ነህ።
11 ዓይኔ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት ያያል፤+
ጆሮዬም የሚያጠቁኝን ክፉ ሰዎች ውድቀት ይሰማል።
13 በይሖዋ ቤት ተተክለዋል፤
በአምላካችን ቅጥር ግቢዎች ያብባሉ።+
እሱ ዓለቴ ነው፤+ በእሱም ዘንድ ክፋት የለም።