ኤርምያስ
51 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
3 ቀስተኛው ደጋኑን አይወጥር።*
በተጨማሪም ማንም ሰው ጥሩሩን ለብሶ አይነሳ።
ለወጣቶቿ ምንም ዓይነት ርኅራኄ አታሳዩ።+
ሠራዊቷን ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።
4 እነሱም በከለዳውያን ምድር ታርደው፣
በጎዳናዎቿም ላይ ክፉኛ ቆስለው ይወድቃሉ።+
5 እስራኤልና ይሁዳ ከአምላካቸው፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ተለይተው መበለት አልሆኑም።+
ምድራቸው* ግን በእስራኤል ቅዱስ ፊት በበደል ተሞልታለች።
በእሷ በደል የተነሳ አትጥፉ።
ይህ የይሖዋ የበቀል ጊዜ ነውና።
ላደረገችው ነገር የእጇን ይከፍላታል።+
7 ባቢሎን በይሖዋ እጅ ያለች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤
ምድርን ሁሉ አሰከረች።
ዋይ ዋይ በሉላት!+
ለሕመሟ የሚሆን በለሳን ውሰዱላት፤ ምናልባት ትፈወስ ይሆናል።”
9 “ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እሷ ግን ልትፈወስ አልቻለችም።
ትታችኋት ሂዱ፤ እያንዳንዳችንም ወደ ገዛ ምድራችን እንሂድ።+
ፍርዷ እስከ ሰማያት ደርሷልና፤
እስከ ደመናት ድረስ ከፍ ብሏል።+
10 ይሖዋ ፍትሕ አስፍኖልናል።+
ኑ፣ የአምላካችንን የይሖዋን ሥራ በጽዮን እንናገር።”+
11 “ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤+ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ።*
ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤+
ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል።
ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና።
12 የባቢሎንን ቅጥሮች ለማጥቃት ምልክት* አቁሙ።+
ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ጠባቂዎችን አቁሙ።
ሽምቅ ተዋጊዎችን አዘጋጁ።
ይሖዋ በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤
በእነሱ ላይ የተናገረውንም ቃል ይፈጽማል።”+
17 እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል።
የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ።
ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።”+
20 “አንቺ ለእኔ እንደ ቆመጥ፣ እንደ ጦር መሣሪያም ነሽ፤
በአንቺ ብሔራትን አደቃለሁ።
በአንቺ መንግሥታትን አወድማለሁ።
21 በአንቺ ፈረሱንና ፈረሰኛውን አደቃለሁ።
በአንቺ የጦር ሠረገላውንና ነጂውን አደቃለሁ።
22 በአንቺ ወንድንና ሴትን አደቃለሁ።
በአንቺ ሽማግሌንና ልጅን አደቃለሁ።
በአንቺ ወጣቱንና ወጣቷን አደቃለሁ።
23 በአንቺ እረኛንና መንጋውን አደቃለሁ።
በአንቺ ገበሬንና ጥማድ ከብቶቹን አደቃለሁ።
በአንቺ ገዢዎችንና የበታች ገዢዎችን አደቃለሁ።
24 ደግሞም በጽዮን፣ በፊታችሁ ለሠሩት ክፋት ሁሉ
ባቢሎንንና የከለዳውያን ምድር ነዋሪዎችን በሙሉ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።
“በአንቺ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ከቋጥኞችም ላይ አንከባልልሻለሁ፤
የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።”
26 “ሰዎች የማዕዘን ድንጋይም ሆነ የመሠረት ድንጋይ ከአንቺ አይወስዱም፤
ምክንያቱም አንቺ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ”+ ይላል ይሖዋ።
በብሔራት መካከል ቀንደ መለከት ንፉ።
በእሷ ላይ እንዲዘምቱ ብሔራትን መድቡ።*
የአራራት፣+ የሚኒ እና የአሽከናዝ መንግሥታት+ እሷን እንዲወጉ ሰብስቧቸው።
በላይዋም ወታደሮችን የሚመለምል መኮንን ሹሙባት።
ፈረሶችንም እንደ ኩብኩባ ስደዱባት።
30 የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋት አቁመዋል።
በምሽጎቻቸው ውስጥ ይቀመጣሉ።
ጉልበት ከድቷቸዋል።+
እንደ ሴት ሆነዋል።+
መኖሪያዎቿ በእሳት ነደዋል።
መቀርቀሪያዎቿ ተሰብረዋል።+
31 ከተማው በየአቅጣጫው እንደተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር
አንዱ መልእክተኛ ሲሮጥ ከሌላው መልእክተኛ ጋር፣
አንዱም ወሬ ነጋሪ ሲሮጥ ከሌላው ወሬ ነጋሪ ጋር ይገናኛል፤+
የደንገል ጀልባዎቹ በእሳት እንደተቃጠሉና
ወታደሮቹ እንደተሸበሩ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።”
33 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“የባቢሎን ሴት ልጅ እንደ አውድማ ናት።
ይህ በኃይል የምትረገጥበት ጊዜ ነው።
በአጭር ጊዜ ውስጥ የመከር ወቅት ይደርስባታል።”
እንደ ባዶ ዕቃ አደረገኝ።
እንደ ትልቅ እባብ ዋጠኝ፤+
የእኔን መልካም ነገሮች በልቶ ሆዱን ሞላ።
በውኃም ጠራርጎ አስወገደኝ።
35 የጽዮን ነዋሪ ‘በእኔና በአካሌ ላይ የተፈጸመው ግፍ በባቢሎን ላይ ይድረስ!’ ትላለች።+
ኢየሩሳሌም ‘ደሜም በከለዳውያን ምድር ነዋሪዎች ላይ ይሁን!’ ትላለች።”
36 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
ባሕሯን አደርቃለሁ፤ የውኃ ጉድጓዶቿንም ደረቅ አደርጋለሁ።+
38 ሁሉም በአንድነት እንደ ደቦል አንበሳ ያገሳሉ።
እንደ አንበሳ ግልገሎች ያጉረመርማሉ።”
39 “ፍላጎታቸው በኃይል ሲነሳሳ እጅግ ደስ እንዲሰኙ
ድግሳቸውን አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋለሁ፤+
ከዚያም ጨርሶ ላይነቁ
እስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ”+ ይላል ይሖዋ።
40 “እንደ ጠቦቶች፣
እንደ አውራ በጎችም ከፍየሎች ጋር ወደሚታረዱበት ቦታ አወርዳቸዋለሁ።”
ባቢሎን በብሔራት መካከል ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!
42 ባሕሩ ባቢሎንን አጥለቅልቋታል።
በማዕበሉ ብዛት ተሸፍናለች።
43 ከተሞቿ አስፈሪ ቦታ እንዲሁም ውኃ የሌለበት ምድርና በረሃ ሆነዋል።
ማንም ሰው የማይኖርበትና አንድም ሰው የማያልፍበት ምድር ሆነዋል።+
ብሔራት ከእንግዲህ ወደ እሱ አይጎርፉም፤
የባቢሎንም ቅጥር ይፈርሳል።+
45 ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከሏ ውጡ!+
ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ+ ሕይወታችሁን* ለማትረፍ ሽሹ!+
46 በምድሪቱ ላይ በሚሰማው ወሬ ልባችሁ አይሸበር፤ በፍርሃትም አትዋጡ።
በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ስለመኖሩ፣
ገዢም በገዢ ላይ ስለመነሳቱ፣ በአንደኛው ዓመት አንድ ወሬ ይሰማል፤
በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሌላ ወሬ ይናፈሳል።
47 ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴን
በባቢሎን የተቀረጹ ምስሎች ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል።
ምድሪቱ በሙሉ ኀፍረት ትከናነባለች፤
የታረዱባትም ሰዎች ሁሉ በመካከሏ ይወድቃሉ።+
49 “ባቢሎን ተጠያቂ የሆነችው ታርደው ለወደቁት እስራኤላውያን ብቻ አይደለም፤+
ከዚህ ይልቅ ከመላው ምድር የመጡ ሰዎችም በባቢሎን ታርደው ወድቀዋል።
50 እናንተ ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ መንገዳችሁን ቀጥሉ፤ ፈጽሞ አትቁሙ!+
በሩቅ ቦታ ሆናችሁ ይሖዋን አስታውሱ፤
ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።”+
51 “ዘለፋውን ስለሰማን በኀፍረት ተውጠናል።
54 “ስሙ! ከባቢሎን ጩኸት፣+
ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል፤+
55 ይሖዋ ባቢሎንን ያጠፋልና፤
ታላቅ ድምፅዋን ጸጥ ያሰኛል፤
ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኃዎች ያስተጋባል።
የድምፃቸው ጩኸት ይሰማል።
በእርግጥ ብድራትን ይመልሳል።+
57 መኳንንቷንና ጥበበኞቿን፣
ገዢዎቿንና የበታች ገዢዎቿን እንዲሁም ተዋጊዎቿን አሰክራለሁ፤+
እነሱም ጨርሶ ላይነቁ
እስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ”+ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው ንጉሥ።
58 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“የባቢሎን ቅጥር ሰፊ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፤+
በሮቿ ረጃጅም ቢሆኑም በእሳት ይጋያሉ።
ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤
ብሔራትም እሳት ለሚበላው ነገር ራሳቸውን እንዲሁ ያደክማሉ።”+
59 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የማህሴያህ ልጅ፣ የነሪያህ+ ልጅ ሰራያህ ከንጉሡ ጋር ወደ ባቢሎን በተጓዘ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለእሱ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ሰራያህ የቤተ መንግሥት አስተዳዳሪ ነበር። 60 ኤርምያስ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ፣ ደግሞም በባቢሎን ላይ ስለሚደርሰው ነገር የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው። 61 በተጨማሪም ኤርምያስ ሰራያህን እንዲህ አለው፦ “ባቢሎን ስትደርስና ከተማዋን ስታይ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብ። 62 ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ይህች ስፍራ እንደምትጠፋና ሰውም ሆነ እንስሳ፣ አንድም የሚኖርባት እንደማይገኝ፣ እንዲሁም ለዘላለም ባድማ እንደምትሆን ተናግረሃል።’+ 63 ይህን መጽሐፍ አንብበህ ከጨረስክ በኋላም መጽሐፉን ከድንጋይ ጋር አስረህ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ወርውረው። 64 ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ባቢሎን በእሷ ላይ ከማመጣው ጥፋት የተነሳ እንዲህ ትሰምጣለች፤ ዳግመኛም አትነሳም፤+ እነሱም ይዝላሉ።’”+
የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል።