ኢሳይያስ
34 እናንተ ብሔራት፣ ለመስማት ወደዚህ ቅረቡ፤
እናንተ ሕዝቦች፣ በትኩረት አዳምጡ።
ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣
ምድርና ከእሷ የሚገኘው ምርት ሁሉ ይስሙ።
ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤
ለእርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።+
4 የሰማያት ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፤
ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ።
ደርቆ እንደረገፈ የወይን ቅጠልና
ደርቆ እንደወደቀ በለስ
ሠራዊታቸውም ሁሉ ደርቀው ይረግፋሉ።
በኤዶም ይኸውም እንዲጠፋ
ፍርድ ባስተላለፍኩበት ሕዝብ ላይ ትወርዳለች።+
6 ይሖዋ ሰይፍ አለው፤ ሰይፉም በደም ትሸፈናለች።
በኤዶምም ምድር
ታላቅ እርድ ያዘጋጃልና።+
7 የዱር በሬዎች ከእነሱ ጋር ይወድቃሉ፤
ወይፈኖችም ከብርቱ ኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ።
ምድራቸውም በደም ይሸፈናል፤
አፈራቸውም በስብ ይርሳል።”
10 እሳቱ በሌሊትም ሆነ በቀን አይጠፋም፤
ጭሷም ለዘላለም ይወጣል።
ከትውልድ እስከ ትውልድም እንደወደመች ትቀራለች፤
ለዘላለም ማንም በእሷ አያልፍም።+
አምላክ፣ ምድሪቱ ባዶ እንደምትሆንና እንደምትጠፋ ለማሳየት
በመለኪያ ገመድና በቱንቢ* ይለካታል።
12 ከታላላቅ ሰዎቿ መካከል ለንግሥና የሚበቃ አንድም ሰው አይኖርም፤
መኳንንቷም ሁሉ ይጠፋሉ።
13 በማይደፈሩ ማማዎቿ ላይ እሾህ፣
በምሽጎቿም ላይ ሳማና ኩርንችት ይበቅላል።
የቀበሮዎች ማደሪያ፣+
የሰጎኖችም መኖሪያ ትሆናለች።
የሌሊት ወፍ በዚያ ታርፋለች፤ ማረፊያ ስፍራም ታገኛለች።
15 ተወንጫፊ እባብ በዚያ ጎጆዋን ትሠራለች፤ እንቁላልም ትጥላለች፤
ከዚያም ትቀፈቅፋለች፤ በጥላዋም ሥር ትሰበስባቸዋለች።
ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው በዚያ ይሰበሰባሉ።
16 በይሖዋ መጽሐፍ ውስጥ ፈልጉ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ አንብቡ፤
ከእነሱ መካከል አንዳቸውም አይጎድሉም፤
ሁሉም ተጓዳኝ አያጡም፤
ይህ ትእዛዝ የወጣው ከይሖዋ አፍ ነውና፤
አንድ ላይ የሰበሰባቸውም የእሱ መንፈስ ነው።
እነሱም ለዘለቄታው ይወርሱታል፤
ከትውልድ እስከ ትውልድም በዚያ ይኖራሉ።