የዮሐንስ የመጀመሪያው ደብዳቤ
1 ከመጀመሪያ የነበረውን፣ የሰማነውን፣ በዓይናችን ያየነውን፣ በትኩረት የተመለከትነውንና በእጃችን የዳሰስነውን የሕይወትን ቃል በተመለከተ እንጽፍላችኋለን፤+ 2 (አዎ፣ ይህ ሕይወት ተገልጧል፤ እኛም አይተናል፤ ደግሞም እየመሠከርን ነው፤+ እንዲሁም በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛ የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት+ ለእናንተ እየነገርናችሁ ነው፤) 3 እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ* ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እየነገርናችሁ ነው።+ ደግሞም ይህ ኅብረታችን ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።+ 4 እነዚህን ነገሮች የምንጽፍላችሁ ደስታችን የተሟላ እንዲሆን ነው።
5 ከእሱ የሰማነውና ለእናንተ የምናሳውቀው መልእክት ይህ ነው፦ አምላክ ብርሃን ነው፤+ በእሱም ዘንድ* ጨለማ ፈጽሞ የለም። 6 “ከእሱ ጋር ኅብረት አለን” ብለን እየተናገርን በጨለማ የምንመላለስ ከሆነ እየዋሸን ነው፤ እውነትንም ሥራ ላይ እያዋልን አይደለም።+ 7 ይሁን እንጂ እሱ ራሱ በብርሃን እንዳለ ሁሉ እኛም በብርሃን የምንመላለስ ከሆነ እርስ በርሳችን ኅብረት ይኖረናል፤ እንዲሁም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።+
8 “ኃጢአት የለብንም” ብለን የምንናገር ከሆነ ራሳችንን እያታለልን ነው፤+ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። 9 ኃጢአታችንን የምንናዘዝ ከሆነ እሱ ታማኝና ጻድቅ ስለሆነ ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል፤ እንዲሁም ከክፋት ሁሉ ያነጻናል።+ 10 “ኃጢአት አልሠራንም” ብለን የምንናገር ከሆነ እሱን ውሸታም እያደረግነው ነው፤ ቃሉም በውስጣችን የለም።