መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።*
58 እናንተ የሰው ልጆች፣ ዝም ብላችሁ እያለ ስለ ጽድቅ ልትናገሩ ትችላላችሁ?+
በቅንነትስ መፍረድ ትችላላችሁ?+
5 ድግምተኞቹ ምንም ያህል ችሎታ ቢኖራቸው
ጉበናው ድምፃቸውን አይሰማም።
6 አምላክ ሆይ፣ ጥርሳቸውን ከአፋቸው አርግፍ!
ይሖዋ ሆይ፣ የእነዚህን አንበሶች* መንጋጋ ሰባብር!
7 ፈስሶ እንደሚያልቅ ውኃ ይጥፉ።
አምላክ ደጋኑን ወጥሮ በቀስቶቹ ይጣላቸው።
8 ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤
ፀሐይን ፈጽሞ እንደማያይ ከሴት የተወለደ ጭንጋፍ ይሁኑ።
9 በእሳት የተቀጣጠለው እሾህ ድስታችሁን ሳያሞቀው፣
አምላክ እርጥቡንም ሆነ የሚነደውን ቅርንጫፍ እንደ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደዋል።+
11 በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል።+
በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።”+