ዘኁልቁ
24 በለዓምም ይሖዋ እስራኤልን መባረክ እንደወደደ* ሲያይ ዳግመኛ ድግምት ፍለጋ አልሄደም፤+ ከዚህ ይልቅ ፊቱን ወደ ምድረ በዳ አቀና። 2 በለዓም አሻግሮ ሲመለከት እስራኤል በየነገዱ እንደሰፈረ አየ፤+ ከዚያም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ።+ 3 በመሆኑም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+
“የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣
ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣
4 የአምላክን ቃል የሰማው፣
ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ ያየው
ዓይኖቹ ሳይከደኑ የሰገደው ሰው ቃል ይህ ነው፦+
5 ያዕቆብ ሆይ፣ ድንኳኖችህ፣
እስራኤል ሆይ፣ የማደሪያ ድንኳኖችህ እንዴት ያማሩ ናቸው!+
7 ከሁለቱም አቁማዳዎቹ ውኃ ይንጠባጠባል፤
ዘሩም በብዙ ውኃዎች አጠገብ ተዘርቷል።+
8 አምላክ ከግብፅ አወጣው፤
ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው።
የሚጨቁኑትን ብሔራት ይበላል፤+
አጥንቶቻቸውንም ይቆረጣጥማል፤ በፍላጻዎቹም ያደቃቸዋል።
9 አድብቷል፤ እንደ አንበሳም ተጋድሟል፤
እንደ አንበሳስ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?
አንተን የሚባርኩህ የተባረኩ ናቸው፤
የሚረግሙህም የተረገሙ ናቸው።”+
10 በዚህ ጊዜ ባላቅ በበለዓም ላይ በጣም ተቆጣ። ባላቅም በንቀት እጆቹን አጨብጭቦ በለዓምን እንዲህ አለው፦ “የጠራሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤+ አንተ ግን ይኸው ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው እንጂ ምንም የፈየድከው ነገር የለም። 11 በል አሁን ቶሎ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ። እኔ እንኳ ታላቅ ክብር ላጎናጽፍህ አስቤ ነበር፤+ ይሖዋ ግን ክብር ነፈገህ።”
12 በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች እንዲህ ብዬ ነገሬአቸው አልነበረም? 13 ‘ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከይሖዋ ትእዛዝ ውጭ በገዛ ፈቃዴ* መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ የምናገረው ይሖዋ የሚነግረኝን ብቻ ነው።’+ 14 እንግዲህ አሁን ወደ ሕዝቤ ልሄድ ነው። ይልቅስ መጥተህ ወደፊት* ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።” 15 ስለዚህ ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+
“የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣
ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣+
16 የአምላክን ቃል የሰማው፣
የልዑሉን አምላክ እውቀት የሚያውቀው ሰው ቃል ይህ ነው፤
ዓይኖቹ ሳይከደኑ እየሰገደ ሳለ
ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ አየ፦
17 አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም፤
እመለከተዋለሁ፣ በቅርቡ ግን አይደለም።
19 ከያዕቆብም አንዱ ድል እያደረገ ይወጣል፤+
የተረፉትንም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁሉ ያጠፋል።”
20 አማሌቅንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦
21 ቄናውያንንም+ ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦
“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጎጆህም በቋጥኝ ላይ የተሠራ ነው።
22 ሆኖም አንድ ሰው ቄይንን ያቃጥላታል።
አሦር ማርኮ እስኪወስዳችሁ ድረስ ምን ያህል ትቆዩ ይሆን?”
23 እሱም እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦
“አቤት! አምላክ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ማን ይተርፍ ይሆን?
ሆኖም እሱም ፈጽሞ ይጠፋል።”
25 ከዚያም በለዓም+ ተነስቶ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።