ኢሳይያስ
2 ከዚህ ይልቅ ከአምላካችሁ ያለያያችሁ የገዛ በደላችሁ ነው።+
የፈጸማችሁት ኃጢአት ፊቱን እንዲሰውርባችሁ አድርጎታል፤
እናንተን ለመስማትም ፈቃደኛ አይደለም።+
ከንፈሮቻችሁ ውሸት ይናገራሉ፤+ አንደበታችሁም ክፋትን ያጉተመትማል።
በማይጨበጥ* ነገር ይታመናሉ፤+ ፍሬ ቢስ ነገሮችን ይናገራሉ።
ችግርን ይፀንሳሉ፤ የሚጎዳ ነገርም ይወልዳሉ።+
እንቁላሎቻቸውንም የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤
እንቁላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።
ሥራቸው ጉዳት የሚያስከትል ነው፤
በእጃቸውም የዓመፅ ሥራ አለ።+
የሚያስቡት ጎጂ ሐሳብ ነው፤
በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።+
መንገዳቸውን ጠማማ ያደርጋሉ፤
በዚያም የሚሄድ ሁሉ ሰላምን አያውቅም።+
9 ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤
ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም።
ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤
ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።+
በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤
በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን።
11 ሁላችንም እንደ ድቦች እናጉረመርማለን፤
እንደ ርግቦችም በሐዘን እናልጎመጉማለን።
ፍትሕን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን አላገኘንም፤
መዳንን ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል።
ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፤
በደላችንን በሚገባ እናውቃለን።+
13 ሕግ ተላልፈናል፤ ይሖዋንም ክደናል፤
ለአምላካችን ጀርባችንን ሰጥተናል።
ቁጣን ለባላጋራዎቹ፣ በቀልን ለጠላቶቹ ይከፍላል።+
ለደሴቶችም የሚገባቸውን ዋጋ ይከፍላቸዋል።
21 “በእኔ በኩል ከእነሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ይህ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “በአንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአፍህ ያኖርኩት ቃሌ፣ ከአንተ አፍ ወይም ከልጆችህ* አፍ ወይም ከልጅ ልጆችህ* አፍ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም አይወሰዱም” ይላል ይሖዋ።