150 ያህን አወድሱ!+
አምላክን በተቀደሰ ስፍራው አወድሱት።+
ብርታቱን በሚያሳየው ጠፈር አወድሱት።+
2 ስለ ብርቱ ሥራዎቹ አወድሱት።+
ወደር የለሽ ስለሆነው ታላቅነቱ አወድሱት።+
3 በቀንደ መለከት+ ድምፅ አወድሱት።
በባለ አውታር መሣሪያና በበገና አወድሱት።+
4 በአታሞና+ በሽብሸባ አወድሱት።
በባለ አውታር መሣሪያና+ በዋሽንት+ አወድሱት።
5 በሚያስተጋባ ሲምባል አወድሱት።
ኃይለኛ ድምፅ በሚያወጣ ሲምባል+ አወድሱት።
6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ።
ያህን አወድሱ!+