ኢሳይያስ
14 ይሖዋ ለያዕቆብ ምሕረት ያሳያልና፤+ እስራኤልንም እንደገና ይመርጠዋል።+ በምድራቸው ላይ ያሰፍራቸዋል፤*+ የባዕድ አገር ሰዎችም ከእነሱ ጋር ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃሉ።+ 2 ሕዝቦችም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል፤ የእስራኤልም ቤት በይሖዋ ምድር ላይ ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸው ያደርጓቸዋል፤+ ማርከው የወሰዷቸውንም ይማርካሉ፤ አስገድደው ያሠሯቸው የነበሩትንም* ይገዟቸዋል።
3 ይሖዋ ከሥቃይህ፣ ከጭንቀትህና በላይህ ተጭኖ ከነበረው ከባድ የባርነት ቀንበር ባሳረፈህ ቀን፣+ 4 በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ ብለህ ትተርታለህ፦*
“ሌሎችን አስገድዶ ሲያሠራ የነበረው* እንዴት አበቃለት!
ጭቆናውስ እንዴት አከተመ!+
5 ይሖዋ የክፉዎችን ዘንግ፣
የገዢዎችን በትር ሰብሯል፤+
6 ሕዝቦችን ያለማቋረጥ በቁጣ ሲመታ የነበረውን፣+
ብሔራትን በማያባራ ስደት በቁጣ ሲገዛቸው የቆየውን ሰብሯል።+
7 መላዋ ምድር አርፋለች፤ ከረብሻም ነፃ ሆናለች።
ሕዝቦች በደስታ እልል ብለዋል።+
8 የጥድ ዛፎችና አርዘ ሊባኖሶች እንኳ ሳይቀሩ
በአንተ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት ያደርጋሉ።
‘አንተ ከወደቅክ ጀምሮ
ማንም ዛፍ ቆራጭ በእኛ ላይ አልተነሳም’ ይላሉ።
በሞት የተረቱትን፣ ጨቋኝ የምድር መሪዎች* ሁሉ
በአንተ የተነሳ ቀሰቀሳቸው።
የብሔራትን ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ላይ አስነሳቸው።
10 ሁሉም እንዲህ በማለት ይናገራሉ፤ እንዲህም ይሉሃል፦
‘አንተም እንደ እኛው ደከምክ ማለት ነው?
አንተም እንደ እኛው ሆንክ?
እጮች ከበታችህ እንደ አልጋ ተነጥፈውልሃል፤
የአልጋ ልብስህም ትሎች ናቸው።’
12 አንተ የምታበራ ኮከብ፣ የንጋት ልጅ ሆይ፣
እንዴት ከሰማይ ወደቅክ!
አንተ ብሔራትን ድል ያደረግክ፣
እንዴት ተቆርጠህ ወደ ምድር ወደቅክ!+
13 በልብህ እንዲህ ብለህ ነበር፦ ‘ወደ ሰማያት እወጣለሁ።+
14 ከደመናዎች ከፍታ በላይ እወጣለሁ፤
ራሴንም እንደ ልዑል አምላክ አደርጋለሁ።’
16 የሚያዩህ አተኩረው ይመለከቱሃል፤
በሚገባም ይመረምሩሃል፤ እንዲህም ይላሉ፦
‘ምድርን ሲያንቀጠቅጥ፣
መንግሥታትንም ሲያናውጥ የነበረው ይህ ሰው አይደለም?+
17 ሰው የሚኖርበትን ምድር፣ ምድረ በዳ ያደረገው፣
ከተሞቹንም የገለበጠው፣+
እስረኞቹንም ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ የከለከለው እሱ አይደለም?’+
የክፉ አድራጊዎች ዘር ስም ዳግመኛ አይጠራም።
22 “በእነሱ ላይ እነሳለሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“ከባቢሎን ስምን፣ ቀሪዎችን፣ ልጆችንና ዘርማንዘርን አጠፋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።
23 “የጃርት መኖሪያና ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋት መጥረጊያም እጠርጋታለሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
24 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ሲል ምሏል፦
“ልክ እንዳሰብኩት ይሆናል፤
በወሰንኩትም መሠረት ይፈጸማል።
ቀንበሩ ከላያቸው ላይ ይነሳል፤
ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”+
እጁ ተዘርግቷል፤
ማንስ ሊያጥፈው ይችላል?+
28 ንጉሥ አካዝ በሞተበት+ ዓመት የሚከተለው ፍርድ ተላለፈ፦
29 “ፍልስጤማውያን ሆይ፣ የመቺያችሁ በትር ስለተሰበረ
አንዳችሁም ብትሆኑ ደስ አይበላችሁ።
31 አንተ በር ሆይ፣ አላዝን! አንቺ ከተማ ሆይ፣ ጩኺ!
ፍልስጤማውያን ሆይ፣ ሁላችሁም ተስፋ ትቆርጣላችሁ!
ከሰሜን ጭስ እየመጣ ነውና፤
አንዳቸውም ቢሆኑ ከሰልፉ ተነጥለው ወደ ኋላ አይቀሩም።”
32 ለብሔሩ መልእክተኞች ምን ብለው መመለስ ይገባቸዋል?
‘የጽዮንን መሠረት የጣለው ይሖዋ ነው፤+
በሕዝቡም መካከል ያሉት ችግረኛ ሰዎች እሷን መጠጊያ ያደርጋሉ’ ብለው ይመልሱላቸዋል።