ኢሳይያስ
20 የአሦር ንጉሥ ሳርጎን የላከው ታርታን* ወደ አሽዶድ+ በመጣበት ዓመት አሽዶድን ወግቶ ያዛት።+ 2 በዚያን ጊዜ ይሖዋ የአሞጽ ልጅ በሆነው በኢሳይያስ በኩል እንዲህ ሲል ተናገረ፦+ “ሂድ፣ ማቁን ከወገብህ ላይ አስወግድ፤ ጫማህንም ከእግርህ ላይ አውልቅ።” እሱም እንደተባለው አደረገ፤ ራቁቱንና* ባዶ እግሩንም ተመላለሰ።
3 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብፅና+ በኢትዮጵያ+ ላይ ለሚደርሰው ነገር ምልክትና+ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ለሦስት ዓመት ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደተመላለሰ ሁሉ፣ 4 የአሦር ንጉሥም የግብፅን ምርኮኞችና+ የኢትዮጵያን ግዞተኞች፣ ልጆችንና ሽማግሌዎችን ሳይቀር መቀመጫቸውን ገልቦ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን እየነዳ ይወስዳቸዋል፤ የግብፅንም እርቃን ያጋልጣል።* 5 ተስፋቸውን በጣሉባት በኢትዮጵያና በሚኮሩባት* በግብፅ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ብሎም ያፍራሉ። 6 በዚያም ቀን በዚህ የባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ ‘ተስፋ የጣልንበትን ይኸውም እርዳታ ለማግኘትና ከአሦር ንጉሥ ለመዳን የሸሸንበትን አገር ተመልከቱ! በዚህ ዓይነት እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ማለቱ አይቀርም።”