ኢሳይያስ
29 “ለአርዔል፣* ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ+ ለአርዔል ወዮላት!
በዓመት ላይ ዓመት ጨምሩ፤
ዓመታዊ በዓሎቻችሁን+ ማክበራችሁን ቀጥሉ።
ይህም ሳይታሰብ፣ በቅጽበት ይፈጸማል።+
6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ አንቺ በማዞር
በነጎድጓድ፣ በምድር መናወጥ፣ በታላቅ ድምፅ፣
በውሽንፍር፣ በአውሎ ነፋስና በሚባላ የእሳት ነበልባል ያድንሻል።”+
7 በዚያን ጊዜ አርዔልን የሚወጉ የብሔራት ሠራዊት ሁሉ፣+
ይኸውም ጦርነት የሚከፍቱባት ሁሉ፣
በእሷ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ማማዎችን የሚሠሩና
ጭንቀት ላይ የሚጥሏት ሁሉ
እንደ ሕልም፣ በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናሉ።
8 አዎ፣ የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ቆይቶ
ሲነቃ ግን ረሃቡ እንደማይለቀው* ሁሉ፣
ደግሞም የተጠማ ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ቆይቶ
ሲነቃ ግን ዝሎና ተጠምቶ እንደሚነሳ* ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።
በጽዮን ተራራ ላይ ጦርነት የሚከፍቱ የብሔራት ሠራዊትም ሁሉ
ተመሳሳይ ነገር ይደርስባቸዋል።+
በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰክረዋል፤
በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳግደዋል።
11 የሁሉ ነገር ራእይ እንደታሸገ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል።+ መጽሐፉን ማንበብ ለሚችል ሰው “እባክህ፣ ጮክ ብለህ አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ታሽጓልና አልችልም” ይላል። 12 መጽሐፉንም ማንበብ ለማይችል ሰው “እባክህ፣ ይህን አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ፈጽሞ ማንበብ አልችልም” ይላል።
13 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ ወደ እኔ የሚቀርበው በአፉ ብቻ ነው፤
በከንፈሩም ያከብረኛል፤+
ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤
እኔንም የሚፈራው፣ ሰዎች ያስተማሩትን ትእዛዛት በማክበር ነው።+
14 ስለዚህ እኔ በእነዚህ ሰዎች ላይ ዳግመኛ የሚያስደንቁ ነገሮች አደርጋለሁ፤+
በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እፈጽማለሁ፤
የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ይጠፋል፤
የአስተዋዮቻቸውም ማስተዋል ይሰወራል።”+
15 ዕቅዳቸውን ከይሖዋ ለመሰወር* ከፍተኛ ጥረት ለሚያደርጉ ወዮላቸው!+
“ማን ያየናል?
ማንስ ያውቅብናል?” በማለት
ተግባራቸውን በጨለማ ቦታ ያከናውናሉ።+
ሸክላ ሠሪው እንደ ሸክላው ሊቆጠር ይገባል?+
የተሠራው ነገር ስለ ሠሪው
“እሱ አልሠራኝም” ማለቱ ተገቢ ነው?+
ደግሞስ ዕቃው ሠሪውን
“ማስተዋል የለውም” ይላል?+
19 የዋሆች በይሖዋ እጅግ ሐሴት ያደርጋሉ፤
በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም በእስራኤል ቅዱስ ደስ ይላቸዋል።+
20 ጨቋኙ ያከትምለታልና፤
ጉረኛውም ያበቃለታል፤
ሌሎችን ለመጉዳት አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ሁሉ ይጠፋሉ፤+
21 ሌሎችን በውሸት ቃል በደለኛ የሚያደርጉ፣
በከተማዋ በር፣+ በተሟጋቹ* ላይ ወጥመድ የሚዘረጉና
መሠረተ ቢስ በሆነ ክስ ጻድቁን ሰው ፍትሕ የሚነፍጉ ይጠፋሉ።+
22 ስለዚህ አብርሃምን+ የተቤዠው ይሖዋ ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦
24 በመንፈስ የባዘኑ ማስተዋል ያገኛሉ፤
የሚያጉረመርሙም የሚሰጣቸውን ትምህርት ይቀበላሉ።”