2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘“ስለ ሦስቱ የሞዓብ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም ኖራ ለማግኘት የኤዶምን ንጉሥ አጥንቶች አቃጥሏል።
2 በመሆኑም በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
የቀሪዮትንም+ የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤
ሞዓብ በትርምስ፣
በቀረርቶና በቀንደ መለከት ድምፅ መካከል ይሞታል።+
3 ገዢውን ከመካከሏ አስወግዳለሁ፤
መኳንንቷንም ሁሉ ከእሱ ጋር እገድላለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’
4 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ስለ ሦስቱ የይሁዳ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም የይሖዋን ሕግ ንቀዋል፤
ሥርዓቱንም አልጠበቁም፤+
ይልቁንም አባቶቻቸው በተከተሉት በዚያው ውሸት ስተዋል።+
5 በመሆኑም በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
የኢየሩሳሌምንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።’+
6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ስለ ሦስቱ የእስራኤል ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም ጻድቁን ለብር፣
ድሃውንም ለጥንድ ጫማ ሲሉ ይሸጣሉ።+
7 የችግረኞችን ራስ በምድር አፈር ላይ ይረግጣሉ፤+
የየዋሆችንም መንገድ ይዘጋሉ።+
አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ግንኙነት በመፈጸም
ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።
8 የብድር መያዣ አድርገው በወሰዱት ልብስ+ ላይ በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤+
መቀጫ በማስከፈል ያገኙትን የወይን ጠጅ በአማልክታቸው ቤት ይጠጣሉ።’
9 ‘ይሁንና ቁመቱ እንደ አርዘ ሊባኖስ፣ ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የሆነውን አሞራዊ
በፊታቸው ያጠፋሁት እኔ ነኝ፤+
ከላይ ያለውን ፍሬውንም ሆነ ከታች ያሉትን ሥሮቹን አጠፋሁ።+
10 ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤+
የአሞራዊውንም ምድር እንድትወርሱ
በምድረ በዳ ለ40 ዓመት መራኋችሁ።+
11 ከልጆቻችሁ መካከል አንዳንዶቹን ነቢያት፣+
ከወጣቶቻችሁም መካከል አንዳንዶቹን ናዝራውያን አድርጌ አስነሳሁ።+
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይህን አላደረግኩም?’ ይላል ይሖዋ።
12 ‘እናንተ ግን ናዝራውያኑ የወይን ጠጅ እንዲጠጡ ሰጣችኋቸው፤+
ነቢያቱንም “ትንቢት አትናገሩ” በማለት አዘዛችኋቸው።+
13 ስለዚህ በታጨደ እህል የተሞላ ጋሪ ከሥሩ ያለውን እንደሚያደቅ፣
ባላችሁበት ስፍራ አደቃችኋለሁ።
14 ፈጣኑ ሰው የሚሸሽበት ቦታ አያገኝም፤+
ብርቱ የሆነው ሰው ኃይሉን ይዞ አይቀጥልም፤
ተዋጊውም ሕይወቱን አያድንም።
15 ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤
ፈጣኑም ሮጦ አያመልጥም፤
ፈረሰኛውም ሕይወቱን አያድንም።
16 ከተዋጊዎቹ መካከል እጅግ ደፋር የሆነው እንኳ
በዚያን ቀን ራቁቱን ይሸሻል’+ ይላል ይሖዋ።”