መዝሙር
የዳዊት ማህሌት፤ በይሁዳ ምድረ በዳ በነበረበት ጊዜ።+
63 አምላክ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ዘወትር እጠባበቃለሁ።+
2 ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ አንተን ተመለከትኩ፤
ብርታትህንና ክብርህን አየሁ።+
4 በመሆኑም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አወድስሃለሁ፤
በአንተም ስም እጆቼን ወደ ላይ አነሳለሁ።
9 ሕይወቴን ለማጥፋት* የሚሹ ሰዎች ግን
ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ።
10 ለሰይፍ ስለት አልፈው ይሰጣሉ፤
የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።
11 ንጉሡ ግን በአምላክ ሐሴት ያደርጋል።
በእሱ የሚምል ሰው ሁሉ ይደሰታል፤*
ሐሰትን የሚናገሩ ሰዎች አፍ ይዘጋልና።