መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
68 አምላክ ይነሳ፤ ጠላቶቹ ይበታተኑ፤
የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።+
4 ለአምላክ ዘምሩ፤ ለስሙም የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+
በበረሃማ ሜዳዎች* እየጋለበ ለሚያቋርጠው ለእሱ ዘምሩ።
ግትር የሆኑ ሰዎች* ግን ውኃ በተጠማ ምድር ይኖራሉ።+
9 አምላክ ሆይ፣ ብዙ ዝናብ እንዲዘንብ አደረግክ፤
ለዛለው ሕዝብህ* ብርታት ሰጠኸው።
10 ድንኳኖችህ በተተከሉበት ሰፈር ሕዝብህ ተቀመጠ፤+
አምላክ ሆይ፣ በጥሩነትህ ለድሃው የሚያስፈልገውን ሰጠኸው።
12 የብዙ ሠራዊት ነገሥታት እግሬ አውጭኝ ብለው ይሸሻሉ!+
በቤት የምትቀር ሴትም ምርኮ ትካፈላለች።+
16 እናንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፣
አምላክ መኖሪያው አድርጎ የመረጠውን ተራራ+ በምቀኝነት ዓይን የምታዩት ለምንድን ነው?
አዎ፣ ይሖዋ በዚያ ለዘላለም ይኖራል።+
17 የአምላክ የጦር ሠረገሎች እልፍ አእላፋት፣ ሺህ ጊዜ ሺህ ናቸው።+
ይሖዋ ከሲና ወደ ቅዱሱ ስፍራ መጥቷል።+
ምርኮኞችን ወሰድክ፤
አምላካችን ያህ ሆይ፣ በመካከላቸው ትኖር ዘንድ
19 ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣+
የሚያድነን እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ይወደስ። (ሴላ)
21 አዎ፣ አምላክ የጠላቶቹን ራስ፣
ኃጢአት መሥራታቸውን የማይተዉ ሰዎችንም ፀጉራም አናት ይፈረካክሳል።+
22 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ከባሳን+ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤
ከጥልቅ ባሕር አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤
23 ይህም እግርህ በደም እንዲታጠብ፣+
ውሾችህም የጠላቶችህን ደም እንዲልሱ ነው።”
24 አምላክ ሆይ፣ እነሱ የድል ሰልፍህን ያያሉ፤
ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚያደርገው የድል ጉዞ ነው።+
25 ዘማሪዎቹ ከፊት ሆነው ሲጓዙ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚጫወቱት ሙዚቀኞች ደግሞ ከኋላ ይከተሏቸው ነበር፤+
አታሞ የሚመቱ ወጣት ሴቶችም በመካከላቸው ነበሩ።+
27 የሁሉም ታናሽ የሆነው ቢንያም+ በዚያ ሰዎችን ይገዛል፤
የይሁዳ መኳንንትም ከሚንጫጩ ጭፍሮቻቸው ጋር፣
እንዲሁም የዛብሎን መኳንንትና የንፍታሌም መኳንንት በዚያ አሉ።
28 አምላካችሁ ብርቱዎች እንድትሆኑ አዟል።
ለእኛ ስትል እርምጃ የወሰድከው አምላክ ሆይ፣ ብርታትህን አሳይ።+
ይሁንና ጦርነት የሚያስደስታቸውን ሕዝቦች ይበታትናል።
32 እናንተ የምድር መንግሥታት ሆይ፣ ለአምላክ ዘምሩ፤+
ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ (ሴላ)
33 ከጥንት ጀምሮ በነበሩት ሰማየ ሰማያት ላይ ለሚጋልበው ዘምሩ።+
እነሆ፣ እሱ በኃያል ድምፁ ያስገመግማል።
34 ለአምላክ ብርታት እውቅና ስጡ።+
ግርማዊነቱ በእስራኤል ላይ ነው፤
ብርታቱም በሰማያት* ውስጥ ነው።
35 አምላክ ከታላቅ መቅደሱ ሲወጣ፣* ፍርሃት* ያሳድራል።+
እሱ ለሕዝቡ ብርታትና ኃይል የሚሰጥ
የእስራኤል አምላክ ነው።+
አምላክ ይወደስ።