መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የዳዊት መዝሙር።
36 ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤
በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።+
2 ስህተቱ ምን እንደሆነ ተረድቶ የሠራውን ነገር እንዳይጠላው፣
ለራሱ ባለው አመለካከት ራሱን እጅግ ይሸነግላልና።+
3 ከአፉ የሚወጣው የክፋትና የሽንገላ ቃል ነው፤
መልካም ነገር ለማድረግ ማስተዋል የለውም።
4 በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል።
ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤
መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም።
5 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ እስከ ሰማያት፣+
ታማኝነትህ እስከ ደመናት ይደርሳል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰውንና እንስሳን ትጠብቃለህ።*+
7 አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!+
የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።+
10 ለሚያውቁህ ታማኝ ፍቅርህን፣
ቀና ልብ ላላቸው ደግሞ ጽድቅህን ዘወትር አሳያቸው።+
11 የትዕቢተኛ እግር እንዲረግጠኝ፣
ወይም የክፉዎች እጅ እንዲያፈናቅለኝ አትፍቀድ።
12 ክፉ አድራጊዎች የት እንደወደቁ ተመልከት፤
ተመተው ወድቀዋል፤ መነሳትም አይችሉም።+