የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 26
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ካህናት ኢየሱስን ለመግደል አሴሩ (1-5)

      • አንዲት ሴት ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት በኢየሱስ ላይ አፈሰሰች (6-13)

      • የመጨረሻው ፋሲካና ይሁዳ የፈጸመው ክህደት (14-25)

      • የጌታ ራት ተቋቋመ (26-30)

      • ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ እንደሚክደው ተናገረ (31-35)

      • ኢየሱስ በጌትሴማኒ ጸለየ (36-46)

      • ኢየሱስ ተያዘ (47-56)

      • በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት ለፍርድ ቀረበ (57-68)

      • ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው (69-75)

ማቴዎስ 26:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የማለፍ በዓል።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:14፤ ማር 14:1, 2፤ ሉቃስ 22:1, 2፤ ዮሐ 13:1
  • +ማቴ 16:21፤ 20:18, 19፤ 27:26፤ ማር 15:15፤ ዮሐ 19:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:57፤ ሉቃስ 3:2፤ ዮሐ 11:49፤ 18:13, 24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለማሰርና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 2:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:3-9፤ ዮሐ 12:1-8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    በቢታንያ በስምዖን ቤት የተደረገ ግብዣ

    jy ምዕ. 101

    ቢታንያ በሚገኘው የስምዖን ቤት ውስጥ

    gt ምዕ. 101

ማቴዎስ 26:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    በቢታንያ በስምዖን ቤት የተደረገ ግብዣ

    jy ምዕ. 101

    ይህን ያውቁ ኖሯል?

    w08 5/1 ገጽ 31

    ይሖዋ አድናቂ አምላክ ነው

    w07 2/1 ገጽ 20

    ቢታንያ በሚገኘው የስምዖን ቤት ውስጥ

    gt ምዕ. 101

ማቴዎስ 26:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአንባብያን ጥያቄዎች

    w00 4/15 ገጽ 31

ማቴዎስ 26:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:11
  • +ማር 14:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት የሚኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

    mrt ርዕስ 36

    ክርስቶስ—የአምላክ ኃይል

    w15 6/15 ገጽ 5 አን. 7

    ዓለምን በእርግጥ መለወጥ የሚችል ይኖር ይሆን?

    w05 11/1 ገጽ 6-7

ማቴዎስ 26:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:8፤ ዮሐ 12:7

ማቴዎስ 26:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    በሳምንቱ መካከል በምናደርገው ስብሰባ ላይ የሚካተት አዲስ ገጽታ

    mwb17.12 ገጽ 5

ማቴዎስ 26:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:2, 4፤ ዮሐ 13:2
  • +ማር 14:10, 11፤ ሉቃስ 22:3-6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ብር ከተባለው ማዕድን የተሠራ ሳንቲም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 11:57
  • +ዘፀ 21:32፤ ዘካ 11:12፤ ማቴ 27:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው

    lfb ትምህርት 86

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    ጥያቄ 6፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መሲሑ ምን ትንቢት ተናግሯል?

    nwt ገጽ 15

    ይህን ያውቁ ኖሯል?

    w08 9/1 ገጽ 25

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:18፤ 23:15፤ ሉቃስ 22:1
  • +ማር 14:12-16፤ ሉቃስ 22:7-13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ከሚያዝያ 2-8

    mwb18.04 ገጽ 2

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

    jy ምዕ. 115

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ባለ ታሪኮች ስማቸው ያልተጠቀሰው ለምንድን ነው?

    w13 8/1 ገጽ 10

    ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ የማለፍ በዓል ተቃረበ

    gt ምዕ. 112

ማቴዎስ 26:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 16:6
  • +ማር 14:17-21፤ ሉቃስ 22:14

ማቴዎስ 26:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 22:21-23፤ ዮሐ 6:70፤ 13:21, 22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የጌታ ራት

    jy ምዕ. 117

    የመታሰቢያው እራት

    gt ምዕ. 114

ማቴዎስ 26:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 41:9፤ ማር 14:20፤ ሉቃስ 22:21፤ ዮሐ 13:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የጌታ ራት

    jy ምዕ. 117

    የመታሰቢያው እራት

    gt ምዕ. 114

ማቴዎስ 26:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 22:22፤ ዮሐ 17:12
  • +ዘዳ 27:25
  • +ማር 14:21

ማቴዎስ 26:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ይህን ያውቁ ኖሯል?

    w11 6/1 ገጽ 18

ማቴዎስ 26:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 10:16
  • +ማር 14:22፤ ሉቃስ 22:19፤ 1ቆሮ 11:23-26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’

    w13 12/15 ገጽ 23-26 አን. 6-15

    ቅዱስ ቁርባን​—ከሥርዓቱ በስተጀርባ ያለው እውነታ

    w08 4/1 ገጽ 27-28

    ክርስቲያኖች ስለ ቁርባን ሊኖራቸው የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው?

    g99 6/8 ገጽ 24

    ቁርባን

    rs ገጽ 261-262

    “ይህ ሥጋዬ ነው“

    w91 1/15 ገጽ 21

    “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም”​—ምሁራን እውነተኛ ሆኖ አግኝተውታል

    w91 3/1 ገጽ 26-30

ማቴዎስ 26:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:23፤ ሉቃስ 22:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’

    w13 12/15 ገጽ 23 አን. 7

    ቅዱስ ቁርባን​—ከሥርዓቱ በስተጀርባ ያለው እውነታ

    w08 4/1 ገጽ 27-28

    የመታሰቢያው እራት

    gt ምዕ. 114

ማቴዎስ 26:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 1:7፤ ዕብ 9:20, 22
  • +ማቴ 20:28፤ ማር 14:24
  • +ዘፀ 24:8፤ ኤር 31:31፤ ዕብ 7:22
  • +1ቆሮ 10:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የጌታ ራት

    jy ምዕ. 117

    የይሖዋ ምሥክሮች የጌታ ራትን የሚያከብሩበት መንገድ ከሌሎች ሃይማኖቶች የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?

    ijwfq ርዕስ 45

    ‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’

    w13 12/15 ገጽ 25 አን. 12

    ቅዱስ ቁርባን​—ከሥርዓቱ በስተጀርባ ያለው እውነታ

    w08 4/1 ገጽ 27-28

    የጌታ እራት ለአንተ ትልቅ ትርጉም አለው

    w03 4/1 ገጽ 5

    ክርስቲያኖች ስለ ቁርባን ሊኖራቸው የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው?

    g99 6/8 ገጽ 24

    የመታሰቢያው እራት

    gt ምዕ. 114

    ቁርባን

    rs ገጽ 261-262

ማቴዎስ 26:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:25፤ ሉቃስ 22:18

ማቴዎስ 26:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 22:39፤ ዮሐ 18:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ይሖዋ—ከሁሉ የላቀው የጥሩነት ምሳሌ

    w02 1/15 ገጽ 13 አን. 10

ማቴዎስ 26:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 13:7፤ ማር 14:27, 28፤ ዮሐ 16:32

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መሲሑን አገኙት!

    w11 8/15 ገጽ 13 አን. 7

    የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 38—ዘካርያስ

    bsi07 ገጽ 29

ማቴዎስ 26:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 28:7, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ‘ክርስቶስ የነበረው ዓይነት አስተሳሰብ’ አላችሁን?

    w00 2/15 ገጽ 19

ማቴዎስ 26:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:29-31

ማቴዎስ 26:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:30፤ ሉቃስ 22:34፤ ዮሐ 13:38

ማቴዎስ 26:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 22:33

ማቴዎስ 26:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 18:1
  • +ማር 14:32-36፤ ሉቃስ 22:40

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

    jy ምዕ. 123

    በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ

    gt ምዕ. 117

ማቴዎስ 26:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 53:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

    jy ምዕ. 123

    በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ

    gt ምዕ. 117

    “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው”

    w96 5/15 ገጽ 21

ማቴዎስ 26:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝናለች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:34

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

    jy ምዕ. 123

    አምላክን በፈቃደኛነት መንፈስ አገልግሉ

    w00 11/15 ገጽ 22-23

    በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ

    gt ምዕ. 117

ማቴዎስ 26:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 20:22፤ ዮሐ 18:11
  • +ማር 14:36፤ ሉቃስ 22:42፤ ዮሐ 5:30፤ 6:38፤ ዕብ 10:9
  • +ዕብ 5:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ቤዛው ምን ያስተምረናል?

    w25.01 ገጽ 23 አን. 10

    እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

    jy ምዕ. 123

    በሕይወትህ ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ቦታ የምትሰጠው ለማን ነው?

    w11 5/15 ገጽ 18 አን. 12

    አምላክን በፈቃደኛነት መንፈስ አገልግሉ

    w00 11/15 ገጽ 22-23

    በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ

    gt ምዕ. 117

    ሥላሴ

    rs ገጽ 406 አን. 4

    መልስ የሚያገኙት የእነማን ጸሎቶች ናቸው?

    w91 9/15 ገጽ 5-6

ማቴዎስ 26:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:37-42፤ ሉቃስ 22:45

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ‘ተግታችሁ ጠብቁ’!

    w03 1/1 ገጽ 20

    “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው”

    w96 5/15 ገጽ 21

ማቴዎስ 26:41

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈቃደኛ።”

  • *

    የሰው ዘር ኃጢአተኛና ፍጽምና የጎደለው መሆኑን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:13፤ ሉቃስ 22:46
  • +ማር 13:33፤ 1ጴጥ 5:8፤ ራእይ 16:15
  • +ሉቃስ 18:1፤ ሮም 12:12፤ ኤፌ 6:18፤ 1ጴጥ 4:7
  • +ማር 14:38፤ ሮም 7:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ከፈተና ራስህን ጠብቅ

    w24.07 ገጽ 14

    ገርነት—ምን ጥቅሞች አሉት?

    w20.05 ገጽ 18

    እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

    jy ምዕ. 123

    “በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ”

    w13 11/15 ገጽ 4-5

    ነቅቶ በመጠበቅ ረገድ የኢየሱስን ምሳሌ ተከተሉ

    w12 2/15 ገጽ 4 አን. 7

    “ወደ ፈተና እንዳትገቡ”

    kp ገጽ 24-26

    ‘ተግታችሁ ጠብቁ’!

    w03 1/1 ገጽ 20

    አምላክን በፈቃደኛነት መንፈስ አገልግሉ

    w00 11/15 ገጽ 23

    በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ

    gt ምዕ. 117

    “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው”

    w96 5/15 ገጽ 21

ማቴዎስ 26:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:10፤ ዮሐ 12:27

ማቴዎስ 26:44

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    በአትክልቱ ሥፍራ ያሳለፈው ሥቃይ

    gt ምዕ. 117

ማቴዎስ 26:45

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው”

    w96 5/15 ገጽ 21

ማቴዎስ 26:46

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ደፋር መሆን ትችላለህ!

    wcg ገጽ 4-7

    “እነሆ፣ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ”

    cf ምዕ. 4 አን. 22-23

ማቴዎስ 26:47

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:43-47፤ ሉቃስ 22:47-51፤ ዮሐ 18:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ

    jy ምዕ. 124

    በይሁዳ ጠቋሚነት መያዝ

    gt ምዕ. 118

ማቴዎስ 26:48

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ

    jy ምዕ. 124

    በይሁዳ ጠቋሚነት መያዝ

    gt ምዕ. 118

ማቴዎስ 26:50

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 41:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ

    jy ምዕ. 124

ማቴዎስ 26:51

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:47፤ ሉቃስ 22:50፤ ዮሐ 18:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ

    jy ምዕ. 124

    በይሁዳ ጠቋሚነት መያዝ

    gt ምዕ. 118

ማቴዎስ 26:52

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 18:11
  • +ዘፍ 9:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም”

    w18.06 ገጽ 6-7

    ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ በጥብቅ ተከተል

    w05 1/1 ገጽ 11 አን. 18

    ኢየሱስ ክርስቶስ በአንተ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

    w05 3/15 ገጽ 6-7

    ገለልተኝነት

    rs ገጽ 270 አን. 3

ማቴዎስ 26:53

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ሌጌዎን” በጥንት የሮም ወታደራዊ መዋቅር ውስጥ አንድን ትልቅ ክፍለ ሠራዊት ያመለክት ነበር። እዚህ ላይ ቃሉ ብዛትን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 6:17፤ ዳን 7:10፤ ማቴ 4:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም”

    w02 9/1 ገጽ 10 አን. 10-11

ማቴዎስ 26:54

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም”

    w02 9/1 ገጽ 10 አን. 10-11

ማቴዎስ 26:55

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 19:47፤ ዮሐ 18:20
  • +ማር 14:48, 49፤ ሉቃስ 22:52, 53

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአንባቢያን ጥያቄዎች

    w20.03 ገጽ 31

ማቴዎስ 26:56

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቅዱሳን መጻሕፍት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:16-18፤ ኢሳ 53:1-12፤ ዳን 9:26
  • +ዘካ 13:7፤ ማር 14:50፤ ዮሐ 16:32

ማቴዎስ 26:57

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:53, 54፤ ሉቃስ 22:54, 55
  • +ዮሐ 18:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

    jy ምዕ. 125

    ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

    jy ምዕ. 126

    ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

    gt ምዕ. 119

    በሊቀ ካህናቱ ግቢ የተፈጸመ ክህደት

    gt ምዕ. 120

ማቴዎስ 26:58

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 18:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

    jy ምዕ. 126

    ይቅር ባይነትን ከጌታው ተምሯል

    ia ምዕ. 23 አን. 12-13

    ይቅር ባይነትን ከጌታው ተምሯል

    w10 4/1 ገጽ 22-23

    በሊቀ ካህናቱ ግቢ የተፈጸመ ክህደት

    gt ምዕ. 120

ማቴዎስ 26:59

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:55-59

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    በኢፍትሐዊነቱ አቻ የማይገኝለት የፍርድ ሂደት

    w11 4/1 ገጽ 19

ማቴዎስ 26:60

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 27:12፤ 35:11

ማቴዎስ 26:61

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 27:39, 40፤ ዮሐ 2:19፤ ሥራ 6:14

ማቴዎስ 26:62

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:60-65

ማቴዎስ 26:63

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 53:7፤ ሥራ 8:32
  • +ሉቃስ 22:67-71

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

    jy ምዕ. 125

    “ለዝምታ ጊዜ አለው”

    w09 5/15 ገጽ 4

    ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

    gt ምዕ. 119

    “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው”

    w96 5/15 ገጽ 21-22

ማቴዎስ 26:64

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 7:13፤ ዮሐ 1:51
  • +መዝ 110:1፤ ሉቃስ 22:69
  • +ማር 14:62፤ ራእይ 1:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ‘ጠንካራ እምነት የነበረውና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ’

    wcg ምዕ. 48

    ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

    jy ምዕ. 125

    ይህን ያውቁ ኖሯል?

    w11 6/1 ገጽ 18

    ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

    gt ምዕ. 119

ማቴዎስ 26:66

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 24:16፤ ዮሐ 19:7

ማቴዎስ 26:67

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 50:6
  • +ሉቃስ 22:63, 64
  • +ኢሳ 53:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ‘ከዚህ የበለጠ ፍቅር ያለው ማንም የለም’

    cf ምዕ. 17

    ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት አገልጋይ

    w09 1/15 ገጽ 22 አን. 4

    ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶች

    w08 10/1 ገጽ 5

    ይህ መጽሐፍ እምነት ሊጣልበት የሚችል ነውን?

    ba ገጽ 17

ማቴዎስ 26:68

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ይህ መጽሐፍ እምነት ሊጣልበት የሚችል ነውን?

    ba ገጽ 17

ማቴዎስ 26:69

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 14:66-72፤ ሉቃስ 22:54-62፤ ዮሐ 18:15-17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

    jy ምዕ. 126

    በሊቀ ካህናቱ ግቢ የተፈጸመ ክህደት

    gt ምዕ. 120

ማቴዎስ 26:71

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 18:25-27

ማቴዎስ 26:73

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አፍህ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    በሊቀ ካህናቱ ግቢ የተፈጸመ ክህደት

    gt ምዕ. 120

ማቴዎስ 26:74

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

    jy ምዕ. 126

    በሊቀ ካህናቱ ግቢ የተፈጸመ ክህደት

    gt ምዕ. 120

ማቴዎስ 26:75

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:34፤ ማር 14:30፤ ዮሐ 13:38

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

    jy ምዕ. 126

    በሊቀ ካህናቱ ግቢ የተፈጸመ ክህደት

    gt ምዕ. 120

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 26:2ዘፀ 12:14፤ ማር 14:1, 2፤ ሉቃስ 22:1, 2፤ ዮሐ 13:1
ማቴ. 26:2ማቴ 16:21፤ 20:18, 19፤ 27:26፤ ማር 15:15፤ ዮሐ 19:16
ማቴ. 26:3ማቴ 26:57፤ ሉቃስ 3:2፤ ዮሐ 11:49፤ 18:13, 24
ማቴ. 26:4መዝ 2:2
ማቴ. 26:6ማር 14:3-9፤ ዮሐ 12:1-8
ማቴ. 26:11ዘዳ 15:11
ማቴ. 26:11ማር 14:7
ማቴ. 26:12ማር 14:8፤ ዮሐ 12:7
ማቴ. 26:13ማር 14:9
ማቴ. 26:14ማቴ 10:2, 4፤ ዮሐ 13:2
ማቴ. 26:14ማር 14:10, 11፤ ሉቃስ 22:3-6
ማቴ. 26:15ዮሐ 11:57
ማቴ. 26:15ዘፀ 21:32፤ ዘካ 11:12፤ ማቴ 27:3
ማቴ. 26:17ዘፀ 12:18፤ 23:15፤ ሉቃስ 22:1
ማቴ. 26:17ማር 14:12-16፤ ሉቃስ 22:7-13
ማቴ. 26:20ዘዳ 16:6
ማቴ. 26:20ማር 14:17-21፤ ሉቃስ 22:14
ማቴ. 26:21ሉቃስ 22:21-23፤ ዮሐ 6:70፤ 13:21, 22
ማቴ. 26:23መዝ 41:9፤ ማር 14:20፤ ሉቃስ 22:21፤ ዮሐ 13:26
ማቴ. 26:24ሉቃስ 22:22፤ ዮሐ 17:12
ማቴ. 26:24ዘዳ 27:25
ማቴ. 26:24ማር 14:21
ማቴ. 26:261ቆሮ 10:16
ማቴ. 26:26ማር 14:22፤ ሉቃስ 22:19፤ 1ቆሮ 11:23-26
ማቴ. 26:27ማር 14:23፤ ሉቃስ 22:20
ማቴ. 26:28ኤፌ 1:7፤ ዕብ 9:20, 22
ማቴ. 26:28ማቴ 20:28፤ ማር 14:24
ማቴ. 26:28ዘፀ 24:8፤ ኤር 31:31፤ ዕብ 7:22
ማቴ. 26:281ቆሮ 10:16
ማቴ. 26:29ማር 14:25፤ ሉቃስ 22:18
ማቴ. 26:30ሉቃስ 22:39፤ ዮሐ 18:1
ማቴ. 26:31ዘካ 13:7፤ ማር 14:27, 28፤ ዮሐ 16:32
ማቴ. 26:32ማቴ 28:7, 16
ማቴ. 26:33ማር 14:29-31
ማቴ. 26:34ማር 14:30፤ ሉቃስ 22:34፤ ዮሐ 13:38
ማቴ. 26:35ሉቃስ 22:33
ማቴ. 26:36ዮሐ 18:1
ማቴ. 26:36ማር 14:32-36፤ ሉቃስ 22:40
ማቴ. 26:37ኢሳ 53:3
ማቴ. 26:38ማር 14:34
ማቴ. 26:39ማቴ 20:22፤ ዮሐ 18:11
ማቴ. 26:39ማር 14:36፤ ሉቃስ 22:42፤ ዮሐ 5:30፤ 6:38፤ ዕብ 10:9
ማቴ. 26:39ዕብ 5:7
ማቴ. 26:40ማር 14:37-42፤ ሉቃስ 22:45
ማቴ. 26:41ማቴ 6:13፤ ሉቃስ 22:46
ማቴ. 26:41ማር 13:33፤ 1ጴጥ 5:8፤ ራእይ 16:15
ማቴ. 26:41ሉቃስ 18:1፤ ሮም 12:12፤ ኤፌ 6:18፤ 1ጴጥ 4:7
ማቴ. 26:41ማር 14:38፤ ሮም 7:23
ማቴ. 26:42ማቴ 6:10፤ ዮሐ 12:27
ማቴ. 26:47ማር 14:43-47፤ ሉቃስ 22:47-51፤ ዮሐ 18:3
ማቴ. 26:50መዝ 41:9
ማቴ. 26:51ማር 14:47፤ ሉቃስ 22:50፤ ዮሐ 18:10
ማቴ. 26:52ዮሐ 18:11
ማቴ. 26:52ዘፍ 9:6
ማቴ. 26:532ነገ 6:17፤ ዳን 7:10፤ ማቴ 4:11
ማቴ. 26:55ሉቃስ 19:47፤ ዮሐ 18:20
ማቴ. 26:55ማር 14:48, 49፤ ሉቃስ 22:52, 53
ማቴ. 26:56መዝ 22:16-18፤ ኢሳ 53:1-12፤ ዳን 9:26
ማቴ. 26:56ዘካ 13:7፤ ማር 14:50፤ ዮሐ 16:32
ማቴ. 26:57ማር 14:53, 54፤ ሉቃስ 22:54, 55
ማቴ. 26:57ዮሐ 18:13
ማቴ. 26:58ዮሐ 18:16
ማቴ. 26:59ማር 14:55-59
ማቴ. 26:60መዝ 27:12፤ 35:11
ማቴ. 26:61ማቴ 27:39, 40፤ ዮሐ 2:19፤ ሥራ 6:14
ማቴ. 26:62ማር 14:60-65
ማቴ. 26:63ኢሳ 53:7፤ ሥራ 8:32
ማቴ. 26:63ሉቃስ 22:67-71
ማቴ. 26:64ዳን 7:13፤ ዮሐ 1:51
ማቴ. 26:64መዝ 110:1፤ ሉቃስ 22:69
ማቴ. 26:64ማር 14:62፤ ራእይ 1:7
ማቴ. 26:66ዘሌ 24:16፤ ዮሐ 19:7
ማቴ. 26:67ኢሳ 50:6
ማቴ. 26:67ሉቃስ 22:63, 64
ማቴ. 26:67ኢሳ 53:3
ማቴ. 26:69ማር 14:66-72፤ ሉቃስ 22:54-62፤ ዮሐ 18:15-17
ማቴ. 26:71ዮሐ 18:25-27
ማቴ. 26:75ማቴ 26:34፤ ማር 14:30፤ ዮሐ 13:38
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
  • 48
  • 49
  • 50
  • 51
  • 52
  • 53
  • 54
  • 55
  • 56
  • 57
  • 58
  • 59
  • 60
  • 61
  • 62
  • 63
  • 64
  • 65
  • 66
  • 67
  • 68
  • 69
  • 70
  • 71
  • 72
  • 73
  • 74
  • 75
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 26:1-75

የማቴዎስ ወንጌል

26 ኢየሱስ ይህን ሁሉ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ 2 “እንደምታውቁት ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ* ይከበራል፤+ የሰው ልጅም በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አልፎ ይሰጣል።”+

3 በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ+ ተብሎ በሚጠራው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተሰብስበው 4 የተንኮል ዘዴ በመጠቀም ኢየሱስን ለመያዝና* ለመግደል ሴራ ጠነሰሱ።+ 5 ይሁን እንጂ “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይፈጠር በበዓሉ ወቅት መሆን የለበትም” ይሉ ነበር።

6 ኢየሱስ በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን+ ቤት ሳለ 7 አንዲት ሴት በጣም ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እሱ ቀረበች፤ እየበላ ሳለም ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር። 8 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? 9 ይህ ዘይት እኮ በውድ ዋጋ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር።” 10 ኢየሱስ ስለ ምን እየተነጋገሩ እንዳለ አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? እሷ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች። 11 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።+ 12 ይህች ሴት ዘይቱን በሰውነቴ ላይ ስታፈስ እኔን ለቀብር ማዘጋጀቷ ነው።+ 13 እውነት እላችኋለሁ፣ በመላው ዓለም ይህ ምሥራች በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችውም መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”+

14 ከዚህ በኋላ፣ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ+ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ+ 15 “እሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች* ሊሰጡት ተስማሙ።+ 16 ስለዚህ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ነበር።

17 የቂጣ* በዓል+ በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው “ፋሲካን እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።+ 18 እሱም “ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣ ‘መምህሩ “የተወሰነው ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በቤትህ አከብራለሁ” ብሏል’ በሉት” አላቸው። 19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።

20 በመሸም ጊዜ+ ከ12 ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።+ 21 እየበሉ ሳሉም “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ 22 እነሱም በዚህ እጅግ አዝነው ሁሉም ተራ በተራ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እሆን?” ይሉት ጀመር። 23 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር በሳህኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው።+ 24 እርግጥ፣ የሰው ልጅ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው+ ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!+ ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።”+ 25 አሳልፎ ሊሰጠው የተዘጋጀው ይሁዳም “ረቢ፣ እኔ እሆን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።

26 እየበሉም ሳሉ ኢየሱስ ቂጣ አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆረሰው፤+ ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ በመስጠት “እንኩ፣ ብሉ። ይህ ሥጋዬን ያመለክታል” አለ።+ 27 ጽዋ አንስቶም አምላክን ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁም ከዚህ ጠጡ፤+ 28 ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ+ የሚፈሰውን+ ‘የቃል ኪዳን+ ደሜን’+ ያመለክታል። 29 ነገር ግን እላችኋለሁ፦ በአባቴ መንግሥት አዲሱን ወይን ከእናንተ ጋር እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከአሁን በኋላ ከዚህ ወይን አልጠጣም።”+ 30 በመጨረሻ የውዳሴ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ።+

31 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’+ ተብሎ ስለተጻፈ በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ላይ በሚደርሰው ነገር የተነሳ ትሰናከላላችሁ። 32 ከተነሳሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”+ 33 ይሁንና ጴጥሮስ መልሶ “ሌሎቹ ሁሉ በአንተ ምክንያት ቢሰናከሉ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልሰናከልም!” አለው።+ 34 ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።+ 35 ጴጥሮስም “አብሬህ መሞት ቢያስፈልገኝ እንኳ በምንም ዓይነት አልክድህም” አለው።+ የቀሩት ደቀ መዛሙርትም ሁሉ እንደዚሁ አሉ።

36 ከዚያም ኢየሱስ ከእነሱ ጋር ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጣ፤+ ደቀ መዛሙርቱንም “ወደዚያ ሄጄ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።+ 37 ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ከሄደ በኋላ እጅግ ያዝንና ይረበሽ ጀመር።+ 38 ከዚያም “እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ።* እዚህ ሁኑና ከእኔ ጋር ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው።+ 39 ትንሽ ወደ ፊት ራቅ በማለት በግንባሩ ተደፍቶ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ+ ከእኔ ይለፍ። ሆኖም እንደ እኔ ፈቃድ ሳይሆን እንደ አንተ ፈቃድ ይሁን”+ ብሎ ጸለየ።+

40 ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸውና ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ “ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት እንኳ ነቅታችሁ መጠበቅ አልቻላችሁም?+ 41 ወደ ፈተና እንዳትገቡ+ ነቅታችሁ ጠብቁ፤+ ሳታሰልሱም ጸልዩ።+ እርግጥ፣ መንፈስ ዝግጁ* ነው፤ ሥጋ* ግን ደካማ ነው።”+ 42 እንደገናም ሄዶ ለሁለተኛ ጊዜ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ሳልጠጣው ይለፍ። ካልሆነ ግን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም”+ ሲል ጸለየ። 43 ዳግመኛም ተመልሶ ሲመጣ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር ተኝተው አገኛቸው። 44 እንደገናም ትቷቸው ሄደና ለሦስተኛ ጊዜ ስለዚያው ነገር ደግሞ ጸለየ። 45 ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የእንቅልፍና የእረፍት ሰዓት ነው? እነሆ፣ የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል። 46 ተነሱ፣ እንሂድ። እነሆ፣ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።” 47 ገና እየተናገረ ሳለ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የተላኩ ሰይፍና ቆመጥ የያዙ ብዙ ሰዎችም አብረውት ነበሩ።+

48 አሳልፎ የሚሰጠውም “እኔ የምስመው ሰው እሱ ነው፤ ያዙት” በማለት ምልክት ሰጥቷቸው ነበር። 49 ይሁዳም በቀጥታ ወደ ኢየሱስ በመሄድ “ረቢ! ሰላም ለአንተ ይሁን” ብሎ ሳመው። 50 ኢየሱስ ግን “ወዳጄ፣ እዚህ የተገኘህበት ዓላማ ምንድን ነው?” አለው።+ በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ቀርበው ኢየሱስን ያዙት፤ አሰሩትም። 51 ሆኖም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ሰዶ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቆረጠው።+ 52 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፤+ ሰይፍ የሚመዙ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ።+ 53  ለመሆኑ በዚህች ቅጽበት ከ12 ሌጌዎን* የሚበልጡ መላእክት እንዲልክልኝ አባቴን መጠየቅ የማልችል ይመስልሃል?+ 54 እንዲህ ከሆነ ታዲያ፣ እንደዚህ ሊሆን ይገባል የሚሉት ቅዱሳን መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?” 55 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው? በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ አስተምር ነበር፤+ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም።+ 56 ይህ ሁሉ የሆነው ግን በነቢያት መጻሕፍት* የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።”+ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።+

57  ኢየሱስን ያሰሩት ሰዎች ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ወደተሰበሰቡበት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ+ ወሰዱት። 58 ይሁንና ጴጥሮስ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ በርቀት ይከተለው ነበር፤ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላም መጨረሻውን ለማየት ከቤቱ አገልጋዮች ጋር ተቀመጠ።+

59 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ ኢየሱስን ለመግደል በእሱ ላይ የሐሰት የምሥክርነት ቃል እየፈለጉ ነበር።+ 60 ይሁንና ብዙ የሐሰት ምሥክሮች ቢቀርቡም ምንም ማስረጃ አላገኙም።+ በኋላ ሁለት ሰዎች ቀርበው 61 “ይህ ሰው ‘የአምላክን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ ልሠራው እችላለሁ’ ብሏል” አሉ።+ 62 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ቆሞ “ምንም መልስ አትሰጥም? እነዚህ ሰዎች በአንተ ላይ ስለሰጡት ምሥክርነት ምን ትላለህ?” አለው።+ 63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ።+ ሊቀ ካህናቱም “አንተ የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆን አለመሆንህን እንድትነግረን በሕያው አምላክ አስምልሃለሁ!” አለው።+ 64 ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው። ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ከዚህ በኋላ የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለው። 65 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ እንዲህ አለ፦ “አምላክን ተሳድቧል! ከዚህ በላይ ምን ምሥክሮች ያስፈልጉናል? ስድቡን እንደሆነ እናንተም ሰምታችኋል። 66 እንግዲህ ምን ትላላችሁ?” እነሱም “ሞት ይገባዋል”+ ብለው መለሱ። 67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፤+ በቡጢም መቱት።+ ሌሎቹም በጥፊ እየመቱት+ 68 “ክርስቶስ ሆይ፣ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን?” አሉት።

69 ጴጥሮስ ከቤት ውጭ፣ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ወደ እሱ መጥታ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።+ 70 እሱ ግን “ስለ ምን እየተናገርሽ እንዳለ አላውቅም” በማለት በሁሉም ፊት ካደ። 71 ወደ ግቢው መግቢያ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሴት አየችውና በዚያ ለነበሩት ሰዎች “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበር” አለች።+ 72 እሱም “ሰውየውን አላውቀውም!” ብሎ በመማል ዳግመኛ ካደ። 73 ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካባቢው ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን “አነጋገርህ* ያስታውቃል፤ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አሉት። 74 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ሰውየውን አላውቀውም!” በማለት ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ። 75 ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”+ ሲል ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2026)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2026 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ