አሞጽ
9 ይሖዋን ከመሠዊያው በላይ ቆሞ አየሁት፤+ እሱም እንዲህ አለ፦ “የዓምዱን አናት ምታ፤ መሠረቶቹም ይናወጣሉ። አናታቸውን ቁረጥ፤ የቀሩትንም በሰይፍ እገድላቸዋለሁ። የሚሸሽ ሁሉ አያመልጥም፤ ለማምለጥ የሚሞክርም ሁሉ አይሳካለትም።+
3 ቀርሜሎስ አናት ላይ ቢደበቁም
ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ።+
ወደ ታችኛው የባሕር ወለል ወርደው ራሳቸውን ከዓይኔ ቢሰውሩም
በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ።
5 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፣ አገሪቱን* ይነካልና፤
እሷም ትቀልጣለች፤+ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ፤+
ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ ትነሳለች፤
በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ተመልሳ ወደ ታች ትወርዳለች።+
7 ‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች* አይደላችሁም?’ ይላል ይሖዋ።
8 ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤
እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+
ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ።
9 ‘እነሆ፣ እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁና፤
ሰው እህልን በወንፊት እንደሚነፋና
አንዲትም ጠጠር ወደ ምድር እንደማትወድቅ ሁሉ
የእስራኤልንም ቤት በብሔራት ሁሉ መካከል እነፋለሁ።+
10 “ጥፋት አይደርስብንም ወይም ወደ እኛ አይጠጋም” የሚሉ
በሕዝቤ መካከል ያሉ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።’
11 ‘በዚያ ቀን የፈረሰውን የዳዊትን ዳስ አቆማለሁ፤+
በግንቡ ላይ ያሉትን ክፍተቶች እጠግናለሁ፤*
ፍርስራሾቹንም አድሳለሁ፤
በጥንት ዘመን እንደነበረው ዳግም እገነባዋለሁ፤+
12 በመሆኑም ከኤዶምና ስሜ ከተጠራባቸው ብሔራት ሁሉ የቀረውን ይወርሳሉ’+
ይላል ይህን የሚያደርገው ይሖዋ።
13 ‘እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤
‘አራሹ አጫጁ ላይ ይደርስበታል፤
ዘሪውም ወይን ጨማቂው ላይ ይደርስበታል፤+
ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+