መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በንጋት እንስት ርኤም።”* የዳዊት ማህሌት።
እኔን ከማዳን፣ ከደረሰብኝም ሥቃይ የተነሳ የማሰማውን ጩኸት+ ከመስማት
የራቅከው ለምንድን ነው?
2 አምላኬ ሆይ፣ በቀን ደጋግሜ እጣራለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+
በሌሊትም ዝም ማለት አልቻልኩም።
8 “ራሱን ለይሖዋ በአደራ ሰጥቷል። እስቲ እሱ ይታደገው!
በእሱ እጅግ የተወደደ ስለሆነ እሱ ያድነው!”+
9 ከማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤+
በእናቴ ጡት ተማምኜ እንድኖር ያደረግከኝ አንተ ነህ።
10 ስወለድ ጀምሮ ለአንተ በአደራ ተሰጠሁ፤*
ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ።
14 እንደ ውኃ ፈሰስኩ፤
አጥንቶቼ ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ።
17 አጥንቶቼን ሁሉ መቁጠር እችላለሁ።+
እነሱም አዩኝ፤ ትኩር ብለውም ተመለከቱኝ።
19 አንተ ግን ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+
አንተ ብርታቴ ነህ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
23 እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ አወድሱት!
እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት!+
እናንተ የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ ለእሱ ታላቅ አክብሮት አሳዩ።
ለእርዳታ ወደ እሱ በጮኸ ጊዜ ሰምቶታል።+
25 በታላቅ ጉባኤ መካከል አወድስሃለሁ፤+
እሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።
ለዘላለም ተደስታችሁ ኑሩ።*
27 የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ይሖዋን አስታውሰው ወደ እሱ ይዞራሉ።
የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ።+
28 ንግሥና የይሖዋ ነውና፤+
ብሔራትን ይገዛል።
29 በምድር ያሉ ባለጸጎች ሁሉ* ይበላሉ፤ ይሰግዳሉም፤
ወደ አፈር የሚወርዱ ሁሉ በእሱ ፊት ይንበረከካሉ፤
ከእነሱ መካከል አንዳቸውም ሕይወታቸውን* ማቆየት አይችሉም።
30 ዘሮቻቸው ያገለግሉታል፤
መጪው ትውልድ ስለ ይሖዋ ይነገረዋል።
31 መጥተው ጽድቁን ያወራሉ።
ገና ለሚወለድ ሕዝብ ያደረገውን ነገር ይናገራሉ።