መዝሙር
ማህሌት። ለቤቱ ምረቃ የተዘመረ የዳዊት መዝሙር።
2 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ፈወስከኝ።+
በሕይወት አቆይተኸኛል፤ ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ አድነኸኛል።+
4 እናንተ የእሱ ታማኝ አገልጋዮች፣ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤+
ማታ ለቅሶ ቢሆንም ጠዋት ግን እልልታ ይሆናል።+
6 በተረጋጋሁ ጊዜ
“ፈጽሞ አልናወጥም”* አልኩ።
7 ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ ባሳየኸኝ ጊዜ እንደ ተራራ አጠነከርከኝ።+
ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተሸበርኩ።+
8 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ ደጋግሜ ተጣራሁ፤+
ሞገስ ለማግኘትም ይሖዋን አብዝቼ ተማጸንኩ።
9 መሞቴና* ወደ ጉድጓድ* መውረዴ+ ምን የሚያስገኘው ጥቅም አለ?
አፈር ያወድስሃል?+ የአንተንስ ታማኝነት ይናገራል?+
10 ይሖዋ ሆይ፣ ስማኝ፤ ሞገስም አሳየኝ።+
ይሖዋ ሆይ፣ ረዳቴ ሁን።+
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ለዘላለም አወድስሃለሁ።