መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች መዝሙር።+ ማስኪል።*
ብሔራትን ድል አድርገህ አባረርካቸው።+
6 በቀስቴ አልታመንምና፤
ሰይፌም ሊያድነኝ አይችልም።+
7 ከጠላቶቻችን ያዳንከን፣
የሚጠሉንን ሰዎች ያዋረድካቸው አንተ ነህ።+
8 ቀኑን ሙሉ ለአምላክ ውዳሴ እናቀርባለን፤
ስምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን። (ሴላ)
9 አሁን ግን ትተኸናል፤ ደግሞም አዋርደኸናል፤
ከሠራዊታችንም ጋር አብረህ አትወጣም።
10 ከጠላታችን ፊት እንድንሸሽ ታደርገናለህ፤+
የሚጠሉን ሰዎች የፈለጉትን ሁሉ ይወስዱብናል።
11 እንደ በግ እንዲበሉን ለጠላቶቻችን አሳልፈህ ሰጠኸን፤
በብሔራት መካከል በተንከን።+
12 ሕዝብህን በማይረባ ዋጋ ሸጥክ፤+
ከሽያጩ ያገኘኸው ትርፍ የለም።
13 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ አደረግከን፤
በዙሪያችን ያሉት ሁሉ እንዲያላግጡብንና እንዲዘብቱብን አደረግክ።
15 ቀኑን ሙሉ በኀፍረት ተውጫለሁ፤
ውርደትም ተከናንቤአለሁ፤
16 ይህም ከሚሳለቁና ከሚሳደቡ ሰዎች ድምፅ፣
እንዲሁም ከሚበቀለን ጠላታችን የተነሳ ነው።
17 ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደርሷል፤ እኛ ግን አልረሳንህም፤
ቃል ኪዳንህንም አላፈረስንም።+
18 ልባችን አልሸፈተም፤
እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።
19 ይሁንና ቀበሮዎች በሚኖሩበት ቦታ ሰባብረኸናል፤
በድቅድቅ ጨለማም ሸፍነኸናል።
እሱ በልብ ውስጥ ያለውን ሚስጥር ያውቃል።+
22 ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤
እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን።+
23 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። ለምንስ ትተኛለህ?+
ንቃ! ለዘላለም አትጣለን።+
24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?
የደረሰብንን ጉስቁልናና ጭቆና የምትረሳው ለምንድን ነው?
26 እኛን ለመርዳት ተነስ!+