ኢሳይያስ
64 በአንተ የተነሳ ተራሮች ይናወጡ ዘንድ
ምነው ሰማያትን ቀደህ በወረድክ!
2 እሳት ጭራሮን አቀጣጥሎ
ውኃን እንደሚያፈላ ሁሉ፣
ያን ጊዜ ጠላቶችህ ስምህን ያውቃሉ፤
ብሔራትም በፊትህ ይሸበራሉ!
4 ከጥንት ዘመን ጀምሮ፣ እሱን በተስፋ ለሚጠባበቁት* ሲል እርምጃ የወሰደ
ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ የሰማም ሆነ በጆሮው ያዳመጠ
ወይም በዓይኑ ያየ ማንም የለም።+
እነሆ፣ ኃጢአት መሥራታችንን በቀጠልን ጊዜ ተቆጣህ፤+
ይህን ያደረግነውም ለረጅም ጊዜ ነው።
ታዲያ አሁን መዳን ይገባናል?
ሁላችንም እንደ ቅጠል እንጠወልጋለን፤
በደላችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደናል።
8 አሁን ግን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ።+
እባክህ ተመልከተን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነንና።
10 የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል።
ጽዮን ምድረ በዳ፣
ኢየሩሳሌምም ጠፍ ምድር ሆናለች።+
12 ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ እርምጃ ከመውሰድ ትታቀባለህ?
ዝም ብለህስ ታያለህ? ደግሞስ ከልክ በላይ እንድንጎሳቆል ትፈቅዳለህ?+