ሚክያስ
2 “መጥፎ ነገር ለሚሸርቡና
በአልጋቸው ላይ ሆነው ክፉ ነገር ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው!
ጠዋት ሲነጋ ያሰቡትን ይፈጽማሉ፤
ምክንያቱም ይህን የሚያደርጉበት ኃይል በእጃቸው ነው።+
3 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘እነሆ፣ በዚህ ወገን ላይ ጥፋት ላመጣ አስቤአለሁ፤+ እናንተም ከዚህ ጥፋት አታመልጡም።*+
ከእንግዲህ ወዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤+ ይህ የጥፋት ጊዜ ነውና።+
እንዲህ ይላሉ፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል!+
የሕዝቤን ድርሻ ለሌሎች ሰጥቷል፤ ከእኔም ወስዶታል!+
እርሻዎቻችንን ለከዳተኛው ይሰጣል።”
5 ስለዚህ በይሖዋ ጉባኤ ውስጥ፣
ምድሪቷን ለማከፋፈል በገመድ የሚለካ ሰው አይኖርህም።
6 “አትስበኩ!” ብለው ይሰብካሉ፤
“እነዚህን ነገሮች መስበክ አይገባቸውም፤
ውርደት አይደርስብንም!”
7 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣
“የይሖዋ መንፈስ አይታገሥም?
እነዚህንስ ነገሮች ያደረገው እሱ ነው?” ሲባል ሰምተሃል?
ቀና በሆነ መንገድ ለሚሄዱ የገዛ ቃሌ መልካም ነገር አያስገኝም?
8 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የገዛ ሕዝቤ ጠላት ሆኖ ተነስቷል።
ከጦርነት እንደሚመለሱ ሰዎች በልበ ሙሉነት ከሚያልፉት ላይ
የሚያምረውን ጌጥ ከልብሱ ጋር* በይፋ ገፈፋችሁ።
9 የሕዝቤን ሴቶች ከሚያምረው ቤታቸው አፈናቀላችኋቸው፤
ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ።
10 ተነሱና ከዚህ ሂዱ፤ ይህ የማረፊያ ቦታ አይደለምና።
ከርኩሰት የተነሳ+ ጥፋት ይመጣል፤ ጥፋቱም ከባድ ነው።+
11 አንድ ሰው ነፋስንና ማታለያን ተከትሎ ቢሄድና
“ስለ ወይን ጠጅና ስለ መጠጥ እሰብክላችኋለሁ” ብሎ ውሸት ቢናገር
ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ሰባኪ ይሆናል!+