መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።* የዳዊት ማህሌት።
62 ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ።*
መዳን የማገኘው ከእሱ ዘንድ ነው።+
3 አንድን ሰው ለመግደል ጥቃት የምትሰነዝሩበት እስከ መቼ ነው?+
ሁላችሁም እንዳዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ እንደተቃረበም የድንጋይ ቅጥር አደገኛ ናችሁ።*
4 ካለበት ከፍ ያለ ቦታ ሊጥሉት* እርስ በርሳቸው ይማከራሉና፤
በመዋሸት ደስ ይሰኛሉ።
በአፋቸው ይባርካሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ።+ (ሴላ)
6 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤
በምንም ዓይነት አልናወጥም።+
7 የእኔ መዳንና ክብር የተመካው በአምላክ ላይ ነው።
እሱ ጠንካራ ዓለቴና መጠጊያዬ ነው።+
8 ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእሱ ታመኑ።
ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ።+
አምላክ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ)
9 የሰው ልጆች እስትንፋስ ናቸው፤
ሰዎች ከንቱ መመኪያ ናቸው።+
አንድ ላይ ሆነው በሚዛን ሲመዘኑ ከአየር እንኳ ይቀልላሉ።+
10 በዝርፊያ አትታመኑ፤
ወይም በስርቆት እጠቀማለሁ ብላችሁ በከንቱ ተስፋ አታድርጉ።
ሀብታችሁ ቢበዛ ልባችሁን በእሱ ላይ አትጣሉ።+
11 አምላክ አንድ ጊዜ ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፦
ብርታት የአምላክ ነው።+