ኢዮብ
40 ይሖዋ በመቀጠል ኢዮብን እንዲህ አለው፦
2 “ስህተት የሚፈላልግ ሰው፣ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር ሊሟገት ይገባል?+
አምላክን መውቀስ የሚፈልግ እሱ መልስ ይስጥ።”+
3 ኢዮብ ለይሖዋ እንዲህ በማለት መለሰ፦
4 “እነሆ፣ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ።+
ምን ልመልስልህ እችላለሁ?
እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።+
5 አንዴ ተናግሬአለሁ፤ ከአሁን በኋላ ግን የምሰጠው መልስ የለም፤
ሁለተኛ ጊዜም ተናገርኩ፤ ከዚህ በኋላ ግን አልናገርም።”
6 ከዚያም ይሖዋ ከአውሎ ነፋስ ውስጥ ለኢዮብ መለሰለት፦+
7 “እባክህ፣ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤
እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ንገረኝ።+
8 የእኔን ፍትሕ ትጠራጠራለህ?*
አንተ ትክክል ሆነህ ትገኝ ዘንድ እኔን ትኮንናለህ?+
10 እስቲ ራስህን በክብርና በግርማ አስጊጥ፤
ደግሞም ታላቅነትና ሞገስ ተላበስ።
11 ቁጣህ ገንፍሎ ይፍሰስ፤
ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው።
12 ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ አይተህ አዋርደው፤
ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ ጨፍልቃቸው።
15 አንተን እንደፈጠርኩ፣ የፈጠርኩትን ብሄሞትን* ተመልከት።
እንደ በሬ ሣር ይበላል።
16 በወገቡ ውስጥ ያለውን ጉልበት፣
በሆዱም ጡንቻዎች ውስጥ ያለውን ኃይል ተመልከት!
17 ጅራቱን እንደ አርዘ ሊባኖስ ያጠነክረዋል፤
የወርቹም ጅማቶች እርስ በርስ የተጠላለፉ ናቸው።
18 አጥንቶቹ የመዳብ ቱቦዎች ናቸው፤
እግሮቹ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው።
19 እሱ ከአምላክ የፍጥረት ሥራዎች መካከል አውራ ነው፤
በሰይፍ ሊቀርበው የሚችለው ሠሪው ብቻ ነው።
20 የዱር እንስሳት ሁሉ የሚፈነጩባቸው ተራሮች
መብሉን ያበቅሉለታልና።
21 በውኃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር፣
ረግረጋማ በሆነ ቦታ በሚገኙ ቄጠማዎችም ሥር ይተኛል።
22 በውኃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤
በሸለቆ* ውስጥ የሚገኙ የአኻያ ዛፎችም ይከቡታል።
23 ወንዙ ቢናወጥ አይፈራም።
ዮርዳኖስ+ ወደ እሱ ቢጎርፍ አይሸበርም።
24 ዓይኖቹ እያዩ ሊይዘው የሚችል አለ?
ወይስ በአፍንጫው መንጠቆ* ሊያስገባ የሚችል ይኖራል?