ኢዮብ
22 ቴማናዊው ኤሊፋዝ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “ሰው አምላክን ሊጠቅመው ይችላል?
ማስተዋል ያለውስ ሰው ምን ይፈይድለታል?+
4 አክብሮት* ስላሳየህ ይቀጣሃል?
ደግሞስ ፍርድ ቤት ያቀርብሃል?
5 ይህን የሚያደርገው የሠራኸው ክፋት ታላቅ ስለሆነ፣
በደልህም ማብቂያ ስለሌለው አይደለም?+
7 ለደከመው ሰው የሚጠጣ ውኃ አልሰጠህም፤
የራበውንም ሰው ምግብ ነፍገሃል።+
8 ምድሪቱ የኃያል ሰው ንብረት ነች፤+
የታደለም ሰው ይኖርባታል።
9 አንተ ግን መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤
አባት የሌላቸውንም ልጆች* ክንድ ሰብረሃል።
12 አምላክ የሚኖረው ከፍ ባለው ሰማይ አይደለም?
በሰማያት ያሉ ከዋክብትም ሁሉ ምን ያህል ከፍ ያሉ እንደሆኑ ተመልከት።
13 አንተ ግን እንዲህ ብለሃል፦ ‘አምላክ ምን ያውቃል?
በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሊፈርድ ይችላል?
14 በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣
ማየት እንዳይችል ደመናት ይጋርዱታል።’
17 እውነተኛውን አምላክ ‘አትድረስብን!’
ደግሞም ‘ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በእኛ ላይ ምን ሊያደርግ ይችላል?’ ይላሉ።
18 ሆኖም ቤቶቻቸውን በመልካም ነገሮች የሞላው እሱ ነው።
(እንዲህ ዓይነቱ ክፉ ሐሳብ ከእኔ የራቀ ነው።)
19 ጻድቅ ይህን አይቶ ይደሰታል፤
ንጹሕ የሆነውም ሰው ይሳለቅባቸዋል፤ እንዲህም ይላቸዋል፦
20 ‘ተቃዋሚዎቻችን ጠፍተዋል፤
ከእነሱ የቀረውንም እሳት ይበላዋል።’
21 እሱን እወቅ፤ ከእሱም ጋር ሰላም ይኖርሃል፤
እንዲህ ካደረግክ መልካም ነገሮች ታገኛለህ።
22 ሕጉን ከአፉ ተቀበል፤
ቃሉንም በልብህ አኑር።+
23 ሁሉን ቻይ ወደሆነው አምላክ ብትመለስ ትታደሳለህ፤+
ክፋትን ከድንኳንህ ብታርቅ፣
24 ወርቅህን* አፈር ውስጥ፣
የኦፊርንም ወርቅ+ ዓለታማ ሸለቆ* ውስጥ ብትጥል፣
25 ያን ጊዜ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ወርቅና*
ጥራት ያለው ብር ይሆንልሃል።
26 በዚህ ጊዜ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ትሰኛለህና፤
ፊትህንም ወደ አምላክ ቀና ታደርጋለህ።
27 ትለምነዋለህ፤ እሱም ይሰማሃል፤
ስእለትህንም ትፈጽማለህ።
28 ለማድረግ ያሰብከው ነገር ሁሉ ይሳካልሃል፤
በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።
29 በእብሪት ስትናገር ትዋረዳለህና፤
ትሑት የሆነውን* ግን ያድነዋል።
30 እሱ ንጹሕ የሆኑትን ያድናል፤
ስለዚህ እጅህ ንጹሕ ከሆነ በእርግጥ ትድናለህ።”