ኢሳይያስ
38 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሞት አፋፍ ደርሶ ነበር።+ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ+ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህ ስለማይቀር ለቤተሰብህ መመሪያ ስጥ።’”+ 2 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ ፊቱን ወደ ግድግዳው አዙሮ ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀመረ፦ 3 “እባክህ ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትና በሙሉ ልብ+ በፊትህ እንዴት እንደተመላለስኩ እንዲሁም በዓይኖችህ ፊት መልካም የሆነውን ነገር እንዳደረግኩ እንድታስታውስ አጥብቄ እለምንሃለሁ።”+ ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።
4 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኢሳይያስ መጣ፦ 5 “ተመልሰህ ሄደህ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦+ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ።+ እንባህንም አይቻለሁ።+ እነሆ በዕድሜህ* ላይ 15 ዓመት እጨምርልሃለሁ፤+ 6 አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ከተማዋንም እጠብቃታለሁ።+ 7 ይሖዋ የተናገረውን ቃል እንደሚፈጽም የሚያሳየው ይሖዋ የሰጠህ ምልክት ይህ ነው፦+ 8 በአካዝ ደረጃ* ላይ ወደ ታች የወረደውን የፀሐይ ጥላ ወደ ኋላ አሥር ደረጃ እንዲመለስ አደርገዋለሁ።”’”+ በመሆኑም ወደ ታች ወርዶ የነበረው የፀሐይ ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከዳነ በኋላ የጻፈው* ጽሑፍ፦
10 እኔ “በዕድሜዬ አጋማሽ ላይ
ወደ መቃብር* በሮች እገባለሁ።
ቀሪውን የሕይወት ዘመኔን እነፈጋለሁ” አልኩ።
11 እንዲህም አልኩ፦ “በሕያዋን ምድር ያህን፣* አዎ ያህን አላይም።
ሁሉም ነገር ከሕልውና ውጭ በሆነበት ስፍራ ከሚኖሩት ጋር በምሆንበት ጊዜ
የሰው ልጆችን አልመለከትም።+
12 መኖሪያዬ ልክ እንደ እረኛ ድንኳን
ተነቅሎ ተወስዶብኛል።+
ሕይወቴን እንደ ሸማኔ ጠቀለልኩ፤
ተሠርቶ ያለቀ ጨርቅ ከሽመና መሣሪያው ላይ እንደሚቆረጥ እኔንም ይቆርጠኛል።
ከማለዳ አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ ትጨርሰኛለህ።+
13 እስከ ጠዋት ድረስ ራሴን አረጋጋለሁ።
አጥንቶቼን ሁሉ እንደ አንበሳ ይሰባብራል፤
ከማለዳ አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ ትጨርሰኛለህ።+
ወደ ላይ ከመመልከቴ የተነሳ ዓይኖቼ ፈዘዙ፦+
15 እንግዲህ ምን ማለት እችላለሁ?
እሱ አናግሮኛል፤ ምላሽም ሰጥቷል።
16 ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሁሉም ሰው በእነዚህ ነገሮች* በሕይወት ይኖራል፤
በእነሱም የእኔ መንፈስ በሕይወት ይኖራል።
አንተ ጤናዬን ትመልስልኛለህ፤ በሕይወትም ታኖረኛለህ።+
ወደ ጉድጓድ የሚወርዱ በታማኝነትህ ተስፋ ሊያደርጉ አይችሉም።+
19 እኔ ዛሬ እንደማደርገው፣
አንተን ሊያወድስ የሚችለው ሕያው፣ አዎ ሕያው የሆነ ሰው ነው።
አባት ለልጆቹ ስለ አንተ ታማኝነት እውቀት ሊያካፍላቸው ይችላል።+
21 ከዚያም ኢሳይያስ “ሕመሙ እንዲሻለው የደረቀ የበለስ ጥፍጥፍ አምጡና እባጩ ላይ አድርጉለት” አለ።+ 22 ሕዝቅያስ “ወደ ይሖዋ ቤት እንደምወጣ ማወቅ የምችልበት ምልክት ምንድን ነው?” ብሎ ነበር።+