17 ጠብ እያለ ትልቅ ድግስ ከተደገሰበት ቤት ይልቅ
ሰላም ባለበት ደረቅ የዳቦ ቁራሽ መብላት ይሻላል።+
2 ጥልቅ ማስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤
ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።
3 ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+
ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው።+
4 ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤
አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል።+
5 በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤+
በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም።+
6 የልጅ ልጆች የሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፤
አባቶችም ለወንዶች ልጆቻቸው ክብር ናቸው።
7 ለሞኝ ሰው ቀና ንግግር አይስማማውም።+
ለገዢ ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም!+
8 ስጦታ ለባለቤቱ እንደከበረ ድንጋይ ነው፤+
በሄደበት ሁሉ ስኬት ያስገኝለታል።+
9 በደልን ይቅር የሚል ሁሉ ፍቅርን ይሻል፤+
አንድን ጉዳይ ደጋግሞ የሚያወራ ግን የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል።+
10 ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅ+
ማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።+
11 ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤
ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።+
12 የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅ
ግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል።+
13 ማንኛውም ሰው ለመልካም ነገር ክፉ የሚመልስ ከሆነ
ክፉ ነገር ከቤቱ አይጠፋም።+
14 ጠብ መጫር ግድብን ከመሸንቆር ተለይቶ አይታይም፤
ስለዚህ ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ።+
15 ክፉውን ነፃ የሚያደርግ፣ በጻድቁም ላይ የሚፈርድ፣+
ሁለቱም በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።
16 ሞኝ ሰው ጥበብን የራሱ የሚያደርግበት ልብ ከሌለው
ጥበብ የሚያገኝበት መንገድ ቢኖር ምን ይጠቅማል?+
17 እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤+
ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።+
18 ማስተዋል የጎደለው ሰው
በባልንጀራው ፊት እጅ በመጨበጥ ዋስ ለመሆን ይስማማል።+
19 ጠብ የሚወድ ሁሉ በደልን ይወዳል።+
በሩን ወደ ላይ አስረዝሞ የሚሠራ ጥፋትን ይጋብዛል።+
20 ልቡ ጠማማ የሆነ አይሳካለትም፤+
በምላሱም የሚያታልል ጥፋት ይደርስበታል።
21 የሞኝ ልጅ አባት ሐዘን ላይ ይወድቃል፤
የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ልጅ የወለደም ደስታ አይኖረውም።+
22 ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው፤+
የተደቆሰ መንፈስ ግን ኃይል ያሟጥጣል።+
23 ክፉ ሰው ፍትሕን ለማዛባት
በስውር ጉቦ ይቀበላል።+
24 ጥልቅ ግንዛቤ ባለው ሰው ፊት ጥበብ ትገኛለች፤
የሞኝ ሰው ዓይን ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል።+
25 ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤
እናቱም እንድትመረር ያደርጋል።+
26 ጻድቁን መቅጣት መልካም አይደለም።
የተከበሩ ሰዎችንም መግረፍ ትክክል አይደለም።
27 አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤+
ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው።+
28 ሞኝ ሰው እንኳ ዝም ሲል እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል፤
ከንፈሮቹንም የሚዘጋ ማስተዋል እንዳለው ተደርጎ ይታያል።