መዝሙር
የዳዊት ማህሌት።
141 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እጣራለሁ።+
እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስልኝ።+
አንተን ስጣራ በትኩረት ስማኝ።+
3 ይሖዋ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤
በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።+
መከራ በገጠማቸው ወቅትም እንኳ መጸለዬን እቀጥላለሁ።
6 ፈራጆቻቸው ከገደል አፋፍ ቢጣሉም፣
ሕዝቡ ለምናገራቸው ቃላት ትኩረት ይሰጣል፤ ደስ የሚያሰኙ ናቸውና።
7 ሰው ሲያርስና ጓል ሲከሰክስ አፈሩ እንደሚበታተን ሁሉ፣
አጥንቶቻችንም በመቃብር* አፍ ላይ ተበታተኑ።
8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ።+
አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።
ሕይወቴን አትውሰድ።*
9 ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣
ክፉ አድራጊዎች ካስቀመጡብኝ አሽክላም ጠብቀኝ።
10 ክፉዎች አንድ ላይ የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ፤+
እኔ ግን አንድም ነገር ሳይነካኝ አልፋለሁ።