መዝሙር
89 የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ስለተገለጠባቸው መንገዶች ለዘላለም እዘምራለሁ።
ታማኝነትህን ለትውልዶች በሙሉ በአፌ አስታውቃለሁ።
5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣
አዎ፣ በቅዱሳን ጉባኤ ታማኝነትህን ያወድሳሉ።
6 በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?+
ከአምላክ ልጆች*+ መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?
8 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ኃያል ነህ፤
ያህ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+
አንተ በሁሉም ነገር ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ።+
10 አንተ ረዓብን*+ እንደተገደለ ሰው አደቀቅከው።+
በብርቱ ክንድህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።+
15 እልልታ የሚያውቁ ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+
ይሖዋ ሆይ፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች በፊትህ ብርሃን ይመላለሳሉ።
16 በስምህ ቀኑን ሙሉ ሐሴት ያደርጋሉ፤
በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ።
18 ጋሻችን ከይሖዋ ነውና፤
ንጉሣችን ከእስራኤል ቅዱስ ነው።+
19 በዚያን ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮችህ በራእይ ተናገርክ፤ እንዲህም አልክ፦
21 እጄ ይደግፈዋል፤+
ክንዴም ያበረታዋል።
22 ማንኛውም ጠላት አያስገብረውም፤
የትኛውም ክፉ ሰው አይጨቁነውም።+
26 እሱም ‘አንተ አባቴ ነህ፤
አምላኬና አዳኝ ዓለቴ ነህ’+ ብሎ ይጠራኛል።
35 ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁ፤
ዳዊትን አልዋሸውም።+
37 በሰማያት ታማኝ ምሥክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ፣
ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” (ሴላ)
38 ሆኖም አንተ ራስህ ጣልከው፤ ደግሞም ገሸሽ አደረግከው፤+
በተቀባው አገልጋይህ ላይ እጅግ ተቆጣህ።
39 ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን ገሸሽ አደረግክ፤
አክሊሉን* መሬት ላይ በመጣል አረከስከው።
40 በድንጋይ የተገነቡትን ቅጥሮቹን* ሁሉ አፈረስክ፤
ምሽጎቹን የፍርስራሽ ክምር አደረግክ።
41 በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ዘረፉት፤
የጎረቤቶቹም መሳለቂያ ሆነ።+
43 በተጨማሪም ሰይፉን መልሰህበታል፤
በጦርነትም እንዲሸነፍ አደረግክ።
44 ግርማ ሞገሱ እንዲጠፋ አደረግክ፤
ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልከው።
45 የወጣትነት ዕድሜውን አሳጠርክበት፤
ኀፍረትም አከናነብከው። (ሴላ)
46 ይሖዋ ሆይ፣ ራስህን የምትሰውረው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+
ቁጣህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራል?
47 ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አስብ!+
ሰዎችን ሁሉ የፈጠርከው እንዲያው ለከንቱ ነው?
48 ሞትን ጨርሶ ሳያይ በሕይወት ሊኖር የሚችል ሰው ማን ነው?+
50 ይሖዋ ሆይ፣ በአገልጋዮችህ ላይ የተሰነዘረውን ዘለፋ አስታውስ፤
ሰዎች ሁሉ የሰነዘሩብኝን ዘለፋ እንዴት እንደተሸከምኩ* አስብ፤
51 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህ ምን ያህል እንደተሳደቡ አስታውስ፤
የቀባኸውን ሰው እርምጃ ሁሉ እንዴት እንደነቀፉ አስብ።
52 ይሖዋ ለዘላለም ይወደስ። አሜን፣ አሜን።+