መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች መዝሙር።+ በአላሞት ቅኝት።*
2 በመሆኑም በምድር ላይ ነውጥ ቢከሰት፣
ተራሮች ተንደው ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰምጡ አንፈራም፤+
3 ውኃዎቹ ቢያስገመግሙና አረፋ ቢደፍቁ፣+
ተራሮችም ከውኃዎቹ ነውጥ የተነሳ ቢንቀጠቀጡ አንሸበርም። (ሴላ)
5 አምላክ በከተማዋ ውስጥ ነው፤+ እሷም አትንኮታኮትም።
ጎህ ሲቀድ አምላክ ይደርስላታል።+
6 ብሔራት ሁከት ፈጠሩ፤ መንግሥታት ተገለበጡ፤
እሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።+
7 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+
የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው። (ሴላ)
8 ኑና የይሖዋን ሥራዎች እዩ፤
በምድርም ላይ አስደናቂ ነገሮችን እንዴት እንዳከናወነ ተመልከቱ።
ቀስትን ይሰባብራል፤ ጦርንም ያነክታል፤
የጦር ሠረገሎችን* በእሳት ያቃጥላል።
10 “አርፋችሁ ተቀመጡ፤ እኔ አምላክ እንደሆንኩም እወቁ።