ዘኁልቁ
21 በኔጌብ የሚኖረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ+ እስራኤላውያን በአታሪም መንገድ እየመጡ መሆናቸውን በሰማ ጊዜ በእነሱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ከመካከላቸውም የተወሰኑትን በምርኮ ወሰደ። 2 ስለዚህ እስራኤል “ይህን ሕዝብ በእጄ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ከሆነ ከተሞቻቸውን ጠራርጌ አጠፋለሁ” በማለት ለይሖዋ ስእለት ተሳለ። 3 በመሆኑም ይሖዋ የእስራኤልን ጩኸት ሰማ፤ ከነአናውያንንም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ሕዝቡንና ከተሞቻቸውን ጠራርገው አጠፉ። ስለሆነም የቦታውን ስም ሆርማ*+ አሉት።
4 እስራኤላውያን ከሆር ተራራ+ በመነሳት በኤዶም ምድር ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ የቀይ ባሕርን መንገድ ይዘው ተጓዙ፤+ ከጉዞውም የተነሳ ሕዝቡ* ዛለ። 5 ሕዝቡም እንዲህ በማለት በአምላክና በሙሴ ላይ ያማርር ጀመር፦+ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ፣ ውኃ የለ፤+ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል።”*+ 6 በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ መርዘኛ* እባቦችን ሰደደባቸው፤ እባቦቹም ሰዎቹን ስለነደፏቸው ብዙ እስራኤላውያን ሞቱ።+
7 ስለሆነም ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጥቶ “በይሖዋና በአንተ ላይ በማማረራችን ኃጢአት ሠርተናል።+ እባቦቹን ከመካከላችን እንዲያስወግድልን ይሖዋን ተማጸንልን” አለ። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ተማጸነ።+ 8 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመርዛማ* እባብ ምስል ሠርተህ እንጨት ላይ ስቀለው። ማንኛውም ሰው በሚነደፍበት ጊዜ በሕይወት እንዲኖር ምስሉን ማየት አለበት።” 9 ሙሴም ወዲያው የመዳብ እባብ+ ሠርቶ እንጨት ላይ ሰቀለው፤+ አንድ ሰው እባብ ሲነድፈው ከመዳብ ወደተሠራው እባብ ከተመለከተ ይድን ነበር።+
10 ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ከነበሩበት ተነስተው በመጓዝ በኦቦት ሰፈሩ።+ 11 ከዚያም ከኦቦት ተነስተው በምሥራቅ አቅጣጫ በሞዓብ ፊት ለፊት በሚገኘው ምድረ በዳ በኢዬዓባሪም+ ሰፈሩ። 12 ከዚያ ተነስተው ደግሞ በዘረድ ሸለቆ*+ ሰፈሩ። 13 ከዘረድ ሸለቆ ተነስተው ከአሞራውያን ድንበር ጀምሮ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሚገኘው በአርኖን ክልል+ ሰፈሩ፤ ምክንያቱም አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ድንበር ነው። 14 የይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ በማለት የሚናገረው ለዚህ ነው፦ “በሱፋ የሚገኘው ዋሄብ፣ የአርኖን ሸለቆዎች* 15 እንዲሁም ኤር ወደሚገኝበት አቅጣጫ የሚዘረጋውና የሞዓብን ድንበር የሚያዋስነው የሸለቆዎች* ቁልቁለት።”*
16 ከዚያም ወደ በኤር ተጓዙ። ይሖዋ ሙሴን “ሕዝቡን ሰብስብ፤ እኔም ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ያለው ይህን የውኃ ጉድጓድ አስመልክቶ ነው።
17 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ፦
“አንተ ጉድጓድ፣ ውኃ አፍልቅ! እናንተም መልሱለት!*
18 መኳንንት ለቆፈሩት፣ በሕዝቡ መካከል ያሉ ታላላቅ ሰዎች ለማሱት፣
በገዢ ዘንግና በራሳቸው በትሮች ላዘጋጁት የውኃ ጉድጓድ ዘምሩለት።”
ከዚያም ከምድረ በዳው ተነስተው ወደ ማታናህ ተጓዙ፤ 19 ከማታናህ ተነስተው ደግሞ ወደ ናሃሊኤል፣ ከናሃሊኤልም ተነስተው ወደ ባሞት+ ተጓዙ። 20 ከባሞትም ተነስተው የሺሞንን*+ ቁልቁል ማየት ወደሚቻልበት በጲስጋ+ አናት ላይ ወደሚገኘውና በሞዓብ ክልል*+ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ።
21 እስራኤላውያን የአሞራውያን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሲሖን እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፦+ 22 “ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን። ወደ የትኛውም እርሻ ወይም ወደ የትኛውም የወይን ቦታ አንገባም። ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ በንጉሡ መንገድ ቀጥ ብለን እንሄዳለን።”+ 23 ሲሖን ግን እስራኤላውያን ክልሉን አቋርጠው እንዲያልፉ አልፈቀደላቸውም። ከዚህ ይልቅ ሲሖን ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ሄደ፤ ያሃጽ በደረሰ ጊዜም ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ ገጠመ።+ 24 እስራኤላውያን ግን በሰይፍ ድል አደረጉት፤+ ምድሩንም ከአርኖን+ አንስቶ በአሞናውያን አቅራቢያ እስከሚገኘው እስከ ያቦቅ+ ድረስ ያዙ፤+ ሆኖም ያዜር+ የአሞናውያን ወሰን+ ስለሆነ ከዚያ አላለፉም።
25 በመሆኑም እስራኤላውያን እነዚህን ከተሞች ሁሉ ያዙ፤ ከዚያም በአሞራውያን+ ከተሞች ይኸውም በሃሽቦንና በሥሯ* ባሉት ከተሞች ሁሉ መኖር ጀመሩ። 26 ምክንያቱም ሃሽቦን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን ከተማ ነበረች፤ እሱም ከሞዓብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድር ከእጁ ወስዶበት ነበር። 27 እንዲህ የሚለውን ቅኔ በመቀኘት የተሳለቁበት በዚህ የተነሳ ነው፦
“ወደ ሃሽቦን ኑ።
የሲሖን ከተማ ትገንባ፤ ጸንታም ትቁም።
28 እሳት ከሃሽቦን፣ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ ወጥቷልና።
የሞዓብን ኤር፣ የአርኖንን ኮረብቶች ጌቶች በላ።
29 ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! እናንተ የከሞሽ+ ሕዝቦች ሆይ፣ ድምጥማጣችሁ ይጠፋል።
ወንዶች ልጆቹን ለስደት ይዳርጋል፤ ሴቶች ልጆቹንም ለአሞራውያን ንጉሥ ለሲሖን ምርኮኛ አድርጎ ይሰጣል።
31 ስለዚህ እስራኤላውያን በአሞራውያን ምድር መኖር ጀመሩ። 32 ከዚያም ሙሴ ያዜርን እንዲሰልሉ የተወሰኑ ሰዎችን ላከ።+ እነሱም በሥሯ* ያሉትን ከተሞች ተቆጣጠሩ፤ በዚያ የነበሩትንም አሞራውያን አባረሩ። 33 ከዚህ በኋላ ተመልሰው በባሳን መንገድ ወጡ። የባሳን ንጉሥ ኦግም+ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥማቸው ወጣ።+ 34 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤+ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።”+ 35 በመሆኑም ኦግን ከወንዶች ልጆቹና ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አንድም ሰው ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤+ ምድሩንም ወረሱ።+