መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
2 የሚያስገመግም ድምፅ ካለበት ጉድጓድ፣
ከሚያዘቅጥ ማጥም አወጣኝ።
እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆመ፤
አረማመዴንም አጸና።
3 ከዚያም በአፌ ላይ አዲስ መዝሙር፣+
ለአምላካችን የሚቀርብ ውዳሴ አኖረ።
ብዙዎች በፍርሃት* ተውጠው ይመለከታሉ፤
በይሖዋም ይታመናሉ።
የሚቃጠል መባና የኃጢአት መባ እንዲቀርብልህ አልጠየቅክም።+
7 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ መጥቻለሁ።
ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል ተጽፏል።+
9 በታላቅ ጉባኤ መካከል የጽድቅን ምሥራች አውጃለሁ።+
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው፣
እነሆ፣ ከንፈሮቼን አልከለክልም።+
10 ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሽግም።
ታማኝነትህንና ማዳንህን አውጃለሁ።
በታላቅ ጉባኤ መካከል ታማኝ ፍቅርህንና እውነትህን አልደብቅም።”+
11 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህን አትንፈገኝ።
ታማኝ ፍቅርህና እውነትህ ምንጊዜም ይጠብቁኝ።+
12 ለመቁጠር እንኳ የሚያታክት መከራ ከቦኛል።+
13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለማዳን እባክህ ፈቃደኛ ሁን።+
ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
14 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹ ሁሉ፣
ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።
በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙ
አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።
15 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉኝ
በሚደርስባቸው ኀፍረት የተነሳ ክው ይበሉ።
የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣
ምንጊዜም “ይሖዋ ታላቅ ይሁን” ይበሉ።+
17 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤
ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ።