ዘሌዋውያን
2 “‘አንድ ሰው* ለይሖዋ የእህል መባ+ የሚያቀርብ ከሆነ መባው የላመ ዱቄት መሆን አለበት፤ በላዩም ላይ ዘይት ያፍስበት፤ ነጭ ዕጣንም ያስቀምጥበት።+ 2 ከዚያም ካህናት ወደሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ያመጣዋል፤ ካህኑም ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ የላመ ዱቄትና ዘይት፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ይወስዳል፤ ይህንም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። 3 ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤+ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+
4 “‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ የእህል መባ የምታቀርብ ከሆነ ከላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ ወይም ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ* መሆን ይኖርበታል።+
5 “‘መባህ በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ+ ከሆነ በዘይት ከተለወሰ እርሾ ያልገባበት የላመ ዱቄት የተጋገረ መሆን ይኖርበታል። 6 መቆራረስ አለበት፤ ዘይትም አፍስበት።+ ይህ የእህል መባ ነው።
7 “‘መባህ በድስት የተዘጋጀ የእህል መባ ከሆነ ከላመ ዱቄትና ከዘይት የተሠራ መሆን ይኖርበታል። 8 ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል መባ ወደ ይሖዋ ማምጣት ይኖርብሃል፤ ወደ መሠዊያው ለሚያቀርበውም ካህን ይሰጠው። 9 ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ እንዲሆን ከእህል መባው ላይ የተወሰነውን በማንሳት ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ 10 ከእህል መባው የተረፈው የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+
11 “‘እርሾ ወይም ማር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ማጨስ ስለሌለባችሁ ለይሖዋ ከምታቀርቡት የእህል መባ ውስጥ እርሾ የገባበት ምንም ነገር አይኑር።+
12 “‘እነዚህንም የፍሬ በኩራት መባ+ አድርጋችሁ ለይሖዋ ልታቀርቧቸው ትችላላችሁ፤ ሆኖም ደስ እንደሚያሰኝ* መዓዛ ሆነው ወደ መሠዊያው መምጣት የለባቸውም።
13 “‘የምታቀርበው የእህል መባ በሙሉ በጨው መቀመም አለበት፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨውም ከእህል መባህ ላይ አይጥፋ። ከማንኛውም መባህ ጋር ጨው አብረህ ታቀርባለህ።+
14 “‘መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ የደረሰውን ሆኖም ገና እሸት የሆነውን በእሳት የተጠበሰና የተከካ እህል መጀመሪያ ላይ እንደደረሰው ፍሬህ የእህል መባ አድርገህ አቅርብ።+ 15 በላዩም ላይ ዘይት ትጨምርበታለህ፤ ነጭ ዕጣንም ታስቀምጥበታለህ። ይህ የእህል መባ ነው። 16 ካህኑም ከተከካው እህልና ከዘይቱ የተወሰነውን፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ወስዶ አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ያጨሰዋል።