መዝሙር
3 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+
ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+
ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።
5 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣
ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+
6 እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣+
እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።
7 እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+
ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+
8 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፣
የገባውን ቃል* እስከ ሺህ ትውልድ ያስታውሳል፤+
9 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+
ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤+
10 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣
ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤
11 “የከነአንን ምድር
ርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።+
13 እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣
ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+
17 ባሪያ እንዲሆን የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍን
ከእነሱ አስቀድሞ ላከው።+
20 ንጉሡ ልኮ አስፈታው፤+
የሕዝቦቹም ገዢ ነፃ አወጣው።
21 የቤቱ ጌታ አድርጎ ሾመው፤
የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፤+
22 ይህም ደስ ባሰኘው* መንገድ በመኳንንቱ ላይ እንዲሠለጥን፣*
ሽማግሌዎቹንም ጥበብ እንዲያስተምር ነው።+
23 ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ መጣ፤+
ያዕቆብም በካም ምድር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ኖረ።
24 አምላክ ሕዝቡ እየተባዛ እንዲሄድ አደረገ፤+
ከጠላቶቻቸው ይበልጥ ኃያላን አደረጋቸው፤+
25 ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ፣
በአገልጋዮቹም ላይ ያሴሩ ዘንድ የጠላቶቻቸው ልብ እንዲለወጥ ፈቀደ።+
27 እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣
ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።+
28 ጨለማን ላከ፤ ምድሪቱም ጨለመች፤+
እነሱ በቃሉ ላይ አላመፁም።
29 ውኃዎቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤
ዓሣዎቻቸውንም ገደለ።+
31 ተናካሽ ዝንቦች እንዲወሯቸው፣
ትንኞችም በግዛቶቻቸው ሁሉ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።+
33 ወይናቸውንና የበለስ ዛፋቸውን መታ፤
በግዛታቸው ውስጥ ያሉትንም ዛፎች አወደመ።
34 አንበጦች፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኩብኩባዎችም
እንዲወሯቸው አዘዘ።+
35 እነሱ በአገሪቱ የሚገኘውን አትክልት ሁሉ በሉ፤
የምድሪቱንም ምርት ፈጁ።
37 ሕዝቡ ብርና ወርቅ ይዞ እንዲወጣ አደረገ፤+
ከነገዶቹም መካከል የተሰናከለ አልነበረም።
39 እነሱን ለመሸፈን ደመናን ዘረጋ፤+
በሌሊትም ብርሃን እንዲሰጥ እሳትን ላከ።+
42 ለአገልጋዩ ለአብርሃም የገባውን ቅዱስ ቃል አስታውሷልና።+
43 ስለዚህ ሕዝቡን በታላቅ ደስታ፣
የተመረጡ አገልጋዮቹንም በእልልታ አወጣቸው።+
44 የሌሎችን ብሔራት ምድር ሰጣቸው፤+
እነሱም ሌሎች ሕዝቦች ለፍተው ያፈሩትን ወረሱ፤+
45 ይህን ያደረገው ድንጋጌዎቹን እንዲጠብቁ፣+
ሕጎቹንም እንዲያከብሩ ነው።
ያህን አወድሱ!*