ኢዮብ
ታዲያ ለድንግሊቱ ተገቢ ያልሆነ ትኩረት እንዴት እሰጣለሁ?+
2 ለመሆኑ ከላይ ከአምላክ የማገኘው ድርሻ ምንድን ነው?
ከፍ ባለ ስፍራ ከሚኖረው ሁሉን ቻይ አምላክ የማገኘውስ ውርሻ ምንድን ነው?
3 በደለኛ ሰው ጥፋት፣
ክፉ ነገር የሚያደርጉስ መቅሰፍት አይደርስባቸውም?+
4 እሱ መንገዴን ሁሉ አያይም?+
እርምጃዬንስ ሁሉ አይቆጥርም?
5 በውሸት ጎዳና ተመላልሼ* አውቃለሁ?
እግሬ ለማታለል ተጣድፎ ያውቃል?+
11 ይህ አሳፋሪ ምግባር፣
ደግሞም በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበርና።+
ሲጠይቀኝስ ምን መልስ እሰጣለሁ?+
15 እኔን በማህፀን ውስጥ የሠራኝ እነሱንስ አልሠራም?+
ከመወለዳችን በፊት* የሠራን እሱ ራሱ አይደለም?+
16 ድሃ የሆኑ ሰዎች የፈለጉትን ነገር ነፍጌ፣+
ወይም የመበለቲቱ ዓይን እንዲያዝን* አድርጌ ከሆነ፣+
17 ወላጅ አልባ ለሆኑ ልጆች ሳላካፍል፣
የራሴን ምግብ ብቻዬን በልቼ ከሆነ፣+
18 (ወላጅ አልባ የሆነውን ልጅ* ከወጣትነቴ ጀምሮ እንደ አባት ሆኜ አሳድጌዋለሁና፤
19 ሰው የሚለብሰው አጥቶ በብርድ ሲያልቅ፣
ወይም ድሃው ሲታረዝ አይቼ ከሆነ፣+
20 ከጠቦቶቼ የተሸለተውን ፀጉር ለብሶ በሞቀው ጊዜ፣
ሳይባርከኝ ቀርቶ ከሆነ፣+
21 በከተማዋ በር+ ላይ የእኔን እርዳታ በሚፈልግ ወላጅ አልባ ልጅ ላይ*
እጄን በዛቻ አወዛውዤ ከሆነ፣+
22 ክንዴ* ከትከሻዬ ይውለቅ፤
ክንዴም ከክርኔ* ይሰበር።
23 ከአምላክ የሚመጣ ጥፋት ያስፈራኛልና፤
በግርማውም ፊት መቆም አልችልም።
24 ወርቅን መታመኛዬ አድርጌ፣
ወይም ምርጥ የሆነውን ወርቅ ‘አንተ መመኪያዬ ነህ!’ ብዬ ከሆነ፣+
25 ታላቅ ሀብት በማፍራቴ፣
እንዲሁም ብዙ ንብረት በማግኘቴ ደስ ብሎኝ ከሆነ፣+
ወይም ጨረቃ ግርማ ተላብሳ ስትሄድ አይቼ ከሆነ፣+
27 ልቤ በስውር ተታሎ፣
አፌም ለእነሱ አምልኮ ለማቅረብ እጄን ስሞ ከሆነ፣+
28 ይህ በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበር፤
በላይ ያለውን እውነተኛውን አምላክ መካድ ይሆንብኝ ነበርና።
34 የብዙ ሰዎችን ምላሽ በመፍራት፣
ወይም በሌሎች ቤተሰቦች ንቀት በመሸበር፣
ዝም ብያለሁ? ደግሞስ ወደ ውጭ መውጣት ፈርቻለሁ?
በተናገርኩት ነገር ላይ ስሜን አሰፍር ነበር።*
ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ መልስ ይስጠኝ!+
ምነው ከሳሼ ክሱን በሰነድ ላይ ባሰፈረ ኖሮ!
36 በትከሻዬ እሸከመው ነበር፤
እንደ አክሊልም በራሴ ላይ አስረው ነበር።
37 የወሰድኩትን እያንዳንዱን እርምጃ ባሳወቅኩት ነበር፤
እንደ አለቃ በልበ ሙሉነት ወደ እሱ እቀርብ ነበር።
የኢዮብ ቃል እዚህ ላይ ተፈጸመ።