መዝሙር
71 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።
ፈጽሞ ለኀፍረት አልዳረግ።+
2 በጽድቅህ አድነኝ፤ ታደገኝም።
3 ምንጊዜም የምገባበት
መሸሸጊያ ዓለት ሁንልኝ።
አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ስለሆንክ
እኔን ለማዳን ትእዛዝ ስጥ።+
4 አምላኬ ሆይ፣ ከክፉው እጅ፣
ግፈኛ ከሆነው ጨቋኝ ሰው መዳፍ ታደገኝ።+
6 ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ፤
ከእናቴ ማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ።+
ሁልጊዜ አወድስሃለሁ።
7 ለብዙዎች መደነቂያ ሆንኩ፤
አንተ ግን ጽኑ መጠጊያዬ ነህ።
8 አፌ በውዳሴህ ተሞልቷል፤+
ቀኑን ሙሉ ስለ ግርማህ እናገራለሁ።
የሚያድነው ስለሌለ አሳዳችሁ ያዙት።”+
12 አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።
አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
የእኔን ጥፋት የሚሹ
ውርደትና ኀፍረት ይከናነቡ።+
14 እኔ ግን አንተን መጠባበቄን እቀጥላለሁ፤
በውዳሴ ላይ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ።
16 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣
መጥቼ ስለ ብርቱ ሥራዎችህ እናገራለሁ፤
ስለ አንተ ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።
18 አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም እንኳ አትጣለኝ።+
21 ታላቅነቴ ገናና እንዲሆን አድርግ፤
ዙሪያዬንም ከበህ አጽናናኝ።
22 እኔም አምላኬ ሆይ፣ ከታማኝነትህ+ የተነሳ
በባለ አውታር መሣሪያ አወድስሃለሁ።
የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣
በበገና የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።