መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሙትላቤን።* የዳዊት ማህሌት።
א [አሌፍ]
2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤
ልዑል አምላክ ሆይ፣ ለስምህ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+
ב [ቤት]
3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ+
ተሰናክለው ከፊትህ ይጠፋሉ።
4 ለማቀርበው ትክክለኛ ክስ ትሟገትልኛለህና፤
በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ በጽድቅ ትፈርዳለህ።+
ג [ጊሜል]
5 ብሔራትን ገሠጽክ፤+ ክፉውንም አጠፋህ፤
ስማቸውን ለዘላለም ደመሰስክ።
ה [ሄ]
ו [ዋው]
ז [ዛየን]
11 በጽዮን ለሚኖረው ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤
ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አስታውቁ።+
ח [ኼት]
13 ይሖዋ ሆይ፣ ቸርነት አሳየኝ፤
ከሞት ደጆች የምታነሳኝ አምላክ ሆይ፣+ የሚጠሉኝ ሰዎች የሚያደርሱብኝን እንግልት ተመልከት፤
14 ያን ጊዜ የሚያስመሰግኑ ተግባሮችህን በጽዮን ሴት ልጅ ደጆች አውጃለሁ፤+
በማዳን ሥራህም ሐሴት አደርጋለሁ።+
ט [ቴት]
15 ብሔራት፣ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ገቡ፤
የገዛ እግራቸው በስውር ባስቀመጡት መረብ ተያዘ።+
16 ይሖዋ በሚወስደው የፍርድ እርምጃ ይታወቃል።+
ክፉ ሰው በገዛ እጁ በሠራው ነገር ተጠመደ።+
ሂጋዮን።* (ሴላ)
י [ዮድ]
17 ክፉ ሰው፣ አምላክን የሚረሱ ብሔራትም ሁሉ
ወደ መቃብር* ይሄዳሉ።
כ [ካፍ]
19 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! ሟች የሆነ ሰው እንዲያይል አትፍቀድ።
ብሔራት በፊትህ ይፈረድባቸው።+
20 ይሖዋ ሆይ፣ ፍርሃት ልቀቅባቸው፤+
ሕዝቦች ሟች መሆናቸውን ይወቁ። (ሴላ)