ኢዮብ
4 ከዚያም ቴማናዊው ኤሊፋዝ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “አንድ ሰው ሊያናግርህ ቢሞክር ትዕግሥት ታጣለህ?
ደግሞስ ማን ከመናገር ሊቆጠብ ይችላል?
3 እርግጥ ነው፣ አንተ ብዙዎችን ታርም ነበር፤
የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር።
4 ቃልህ የተሰናከለውን ሁሉ ያነሳ ነበር፤
አንተም የሚብረከረኩትን ጉልበቶች ታጸና ነበር።
5 አሁን ግን በአንተ ላይ ሲደርስ ዛልክ፤
በአንተ ላይ ሲመጣ ተደናገጥክ።
6 ለአምላክ ያለህ አክብሮት* መተማመኛህ አይደለም?
ንጹሕ አቋምህን* ጠብቀህ መመላለስህ+ ተስፋ አልሰጠህም?
7 እስቲ ለማስታወስ ሞክር፦ ንጹሕ ከሆኑ ሰዎች መካከል የጠፋ ማን አለ?
ቅኖችስ መቼ ተደምስሰው ያውቃሉ?
9 በአምላክ እስትንፋስ ይጠፋሉ፤
በቁጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።
10 አንበሳ ሊያገሳ፣ የአንበሳም ግልገል ሊያጉረመርም ይችላል፤
ይሁን እንጂ የብርቱ አንበሶች* ጥርስም እንኳ ይሰበራል።
11 አንበሳ የሚታደን ሲያጣ ይጠፋል፤
የአንበሳም ግልገሎች ይበተናሉ።
12 ቃል በስውር መጣልኝ፤
ሹክሹክታውም ወደ ጆሮዬ ደረሰ።
13 ይህም የሆነው ሌሊት ያየሁት ራእይ ባስጨነቀኝ ወቅት፣
ሰዎችም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ በወሰዳቸው ጊዜ ነበር፤
14 በጣም ተንቀጠቀጥኩ፤
አጥንቶቼም ሁሉ በፍርሃት ተዋጡ።
15 መንፈስም በፊቴ አለፈ፤
የገላዬም ፀጉር ቆመ።
16 እሱም ባለበት ቆመ፤
ሆኖም መልኩን መለየት አልቻልኩም።
አንድ ቅርጽ በዓይኔ ፊት ነበር፤
ጸጥታም ሰፍኖ ነበር፤ ከዚያም አንድ ድምፅ ሰማሁ፦
17 ‘ሟች የሆነ ሰው ከአምላክ ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላል?
ሰውስ ከገዛ ሠሪው ይበልጥ ንጹሕ ሊሆን ይችላል?’
20 ከጠዋት እስከ ማታ ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይደቅቃሉ፤
ለዘላለም ይጠፋሉ፤ ደግሞም ማንም ልብ አይላቸውም።
21 ገመዱ እንደተፈታበት ድንኳን አይደሉም?
ያለጥበብ ይሞታሉ።