አንደኛ ዜና መዋዕል
6 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት+ እና ሜራሪ+ ነበሩ። 2 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣+ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ነበሩ። 3 የአምራም+ልጆች* አሮን፣+ ሙሴ+ እና ሚርያም+ ነበሩ። የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛር+ እና ኢታምር+ ነበሩ። 4 አልዓዛር ፊንሃስን+ ወለደ፤ ፊንሃስ አቢሹዓን ወለደ። 5 አቢሹዓ ቡቂን ወለደ፤ ቡቂ ዑዚን ወለደ። 6 ዑዚ ዘራህያህን ወለደ፤ ዘራህያህ መራዮትን ወለደ። 7 መራዮት አማርያህን ወለደ፤ አማርያህ አኪጡብን+ ወለደ። 8 አኪጡብ ሳዶቅን+ ወለደ፤ ሳዶቅ አኪማዓስን+ ወለደ። 9 አኪማዓስ አዛርያስን ወለደ፤ አዛርያስ ዮሃናንን ወለደ። 10 ዮሃናን አዛርያስን ወለደ። እሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም በገነባው ቤት ውስጥ ካህን ሆኖ ያገለግል ነበር።
11 አዛርያስ አማርያህን ወለደ፤ አማርያህ አኪጡብን ወለደ። 12 አኪጡብ ሳዶቅን+ ወለደ፤ ሳዶቅ ሻሉምን ወለደ። 13 ሻሉም ኬልቅያስን+ ወለደ፤ ኬልቅያስ አዛርያስን ወለደ። 14 አዛርያስ ሰራያህን+ ወለደ፤ ሰራያህ የሆጼዴቅን+ ወለደ። 15 ይሖዋ፣ ይሁዳና ኢየሩሳሌም በናቡከደነጾር እጅ በግዞት እንዲወሰዱ ሲያደርግ የሆጼዴቅም በግዞት ተወሰደ።
16 የሌዊ ወንዶች ልጆች ጌርሳም፣* ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ። 17 የጌርሳም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ሊብኒ እና ሺምአይ።+ 18 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ነበሩ። 19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ።
የሌዋውያን ቤተሰቦች በየአባቶቻቸው ስም ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው፦+ 20 ጌርሳም፣+ የጌርሳም ልጅ ሊብኒ፣ የሊብኒ ልጅ ያሃት፣ የያሃት ልጅ ዚማ፣ 21 የዚማ ልጅ ዮአህ፣ የዮአህ ልጅ ኢዶ፣ የኢዶ ልጅ ዛራ፣ የዛራ ልጅ የአትራይ። 22 የቀአት ወንዶች ልጆች፦* አሚናዳብ፣ የአሚናዳብ ልጅ ቆሬ፣+ የቆሬ ልጅ አሲር፣ 23 የአሲር ልጅ ሕልቃና፣ የሕልቃና ልጅ ኤቢያሳፍ፣+ የኤቢያሳፍ ልጅ አሲር፤ 24 የአሲር ልጅ ታሃት፣ የታሃት ልጅ ዑሪኤል፣ የዑሪኤል ልጅ ዖዝያ፣ የዖዝያ ልጅ ሻኡል። 25 የሕልቃና ወንዶች ልጆች አማሳይ እና አሂሞት ነበሩ። 26 ጾፋይ የሕልቃና ልጅ ነበር፤ የጾፋይ ልጅ ናሃት፣ 27 የናሃት ልጅ ኤልያብ፣ የኤልያብ ልጅ የሮሃም እና የየሮሃም ልጅ ሕልቃና+ ነበር። 28 የሳሙኤል+ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ኢዩኤልና ሁለተኛው አቢያህ+ ነበሩ። 29 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፦* ማህሊ፣+ የማህሊ ልጅ ሊብኒ፣ የሊብኒ ልጅ ሺምአይ፣ የሺምአይ ልጅ ዖዛ፣ 30 የዖዛ ልጅ ሺምአ፣ የሺምአ ልጅ ሃጊያህ፣ የሃጊያህ ልጅ አሳያህ።
31 ዳዊት፣ ታቦቱ በይሖዋ ቤት ከተቀመጠ በኋላ በዚያ የሚዘመረውን መዝሙር እንዲመሩ የሾማቸው እነዚህ ነበሩ።+ 32 እነሱ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪገነባ+ ድረስ በማደሪያ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ከመዝሙር ጋር የተያያዘ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ኃላፊነት መሠረት አገልግሎታቸውን ያከናውኑ ነበር።+ 33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር አብረው የሚያገለግሉት ሰዎች እነዚህ ነበሩ፦ ከቀአታውያን መካከል ዘማሪው ሄማን፣+ የኢዩኤል+ ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣ 34 የሕልቃና+ ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ፣ የኤሊዔል ልጅ፣ የቶአ ልጅ፣ 35 የጹፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣ የማሃት ልጅ፣ የአማሳይ ልጅ፣ 36 የሕልቃና ልጅ፣ የኢዩኤል ልጅ፣ የአዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣ 37 የታሃት ልጅ፣ የአሲር ልጅ፣ የኤቢያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣ 38 የይጽሃር ልጅ፣ የቀአት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ ነበር።
39 ወንድሙ አሳፍ+ በቀኙ በኩል ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የቤራክያህ ልጅ፣ የሺምአ ልጅ፣ 40 የሚካኤል ልጅ፣ የባአሴያህ ልጅ፣ የማልኪያህ ልጅ፣ 41 የኤትኒ ልጅ፣ የዛራ ልጅ፣ የአዳያህ ልጅ፣ 42 የኤታን ልጅ፣ የዚማ ልጅ፣ የሺምአይ ልጅ፣ 43 የያሃት ልጅ፣ የጌርሳም ልጅ፣ የሌዊ ልጅ ነበር።
44 ወንድሞቻቸው የሆኑት የሜራሪ+ ዘሮች በስተ ግራ የነበሩ ሲሆን ኤታን+ በዚያ ነበር፤ እሱም የቂሺ ልጅ፣ የአብዲ ልጅ፣ የማሉክ ልጅ፣ 45 የሃሻብያህ ልጅ፣ የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣ 46 የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣ የሼሜር ልጅ፣ 47 የማህሊ ልጅ፣ የሙሺ ልጅ፣ የሜራሪ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ ነበር።
48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው በእውነተኛው አምላክ ቤት፣ በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ሁሉንም አገልግሎት እንዲያከናውኑ ተሹመው ነበር።*+ 49 አሮንና ወንዶች ልጆቹ+ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች ጋር የተያያዙትን ሥራዎች በማከናወን ለእስራኤል ቤት ለማስተሰረይ፣+ የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያና+ በዕጣን መሠዊያው+ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት አቀረቡ። 50 የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፦+ የአሮን ልጅ አልዓዛር፣+ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ፣ የፊንሃስ ልጅ አቢሹዓ፣ 51 የአቢሹዓ ልጅ ቡቂ፣ የቡቂ ልጅ ዑዚ፣ የዑዚ ልጅ ዘራህያህ፣ 52 የዘራህያህ ልጅ መራዮት፣ የመራዮት ልጅ አማርያህ፣ የአማርያህ ልጅ አኪጡብ፣+ 53 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅ፣+ የሳዶቅ ልጅ አኪማዓስ።
54 በክልላቸው ውስጥ በሰፈሮቻቸው* የሚገኙት የመኖሪያ ቦታዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፦ የቀአታውያን ቤተሰብ የሆኑት የአሮን ዘሮች የመጀመሪያው ዕጣ ደረሳቸው፤ 55 በይሁዳ ምድር የምትገኘውን ኬብሮንን+ በዙሪያዋ ካሉት የግጦሽ መሬቶች ጋር ሰጧቸው። 56 ይሁንና የከተማዋን እርሻና ሰፈሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ ሰጡ። 57 ለአሮንም ዘሮች የመማጸኛ ከተሞችን፣*+ ኬብሮንን+ እንዲሁም ሊብናንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ያቲርን፣+ ኤሽተሞዓንና የግጦሽ መሬቶቿን ሰጡ፤+ 58 ሂሌንንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ደቢርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ 59 አሻንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ቤትሼሜሽንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጡ፤ 60 ከቢንያም ነገድም ጌባና+ የግጦሽ መሬቶቿ፣ አለሜትና የግጦሽ መሬቶቿ እንዲሁም አናቶትና+ የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጣቸው። ለወገኖቻቸው የተሰጡት ከተሞቻቸው በአጠቃላይ 13 ከተሞች ነበሩ።+
61 ለቀሩት ቀአታውያን ከሌላው ነገድ ቤተሰብና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ+ ላይ አሥር ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።
62 ለጌርሳማውያን በየቤተሰቦቻቸው ከይሳኮር ነገድ፣ ከአሴር ነገድ፣ ከንፍታሌም ነገድና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ 13 ከተሞች መደቡላቸው።+
63 ለሜራራውያን በየቤተሰቦቻቸው ከሮቤል ነገድ፣ ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድ 12 ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።+
64 በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ለሌዋውያኑ እነዚህን ከተሞች ከነግጦሽ መሬታቸው ሰጧቸው።+ 65 በተጨማሪም ከይሁዳ ነገድ፣ ከስምዖን ነገድና ከቢንያም ነገድ በስማቸው የተጠቀሱትን እነዚህን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።
66 ከቀአታውያን ቤተሰቦች መካከል የተወሰኑት ከኤፍሬም ነገድ ያገኟቸው የራሳቸው የሆኑ ከተሞች ነበሯቸው።+ 67 እነሱም የመማጸኛ ከተሞቹን፣* ተራራማ በሆነው የኤፍሬም ምድር ያለችውን ሴኬምንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ጌዜርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው፤ 68 ዮቅመአምንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ቤትሆሮንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ 69 አይሎንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ጋትሪሞንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው፤ 70 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ደግሞ አኔርንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ቢልአምንና የግጦሽ መሬቶቿን ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች ሰጧቸው።
71 ለጌርሳማውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን የምትገኘውን ጎላንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም አስታሮትንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤+ 72 ከይሳኮር ነገድም ቃዴሽንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ዳብራትንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣+ 73 ራሞትንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም አኔምንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ 74 ከአሴር ነገድም ማሻልንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ አብዶንንና የግጦሽ መሬቶቿን፣+ 75 ሁቆቅንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ሬሆብንና+ የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ 76 ከንፍታሌም ነገድም በገሊላ+ የምትገኘውን ቃዴሽንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ሃሞንንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ቂርያታይምንና የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው።
77 ለቀሩት ሜራራውያን ከዛብሎን+ ነገድ ላይ ሪሞኖንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ታቦርንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ 78 ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፣ በኢያሪኮ ካለው የዮርዳኖስ አካባቢ ከሮቤል ነገድ ላይ በምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼርና የግጦሽ መሬቶቿ፣ ያሃጽና+ የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጧቸው፤ 79 ደግሞም ቀደሞትና+ የግጦሽ መሬቶቿ እንዲሁም መፋአትና የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጧቸው፤ 80 ከጋድ ነገድ ላይ ደግሞ በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ማሃናይምንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ 81 ሃሽቦንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ያዜርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው።