ኢዮብ
24 “ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለምን ጊዜ አልወሰነም?+
እሱን የሚያውቁትስ ቀኑን* ለምን አያዩም?
3 አባት የሌላቸውን ልጆች አህያ እየነዱ ይወስዳሉ፤
የመበለቲቱንም በሬ መያዣ አድርገው ይወስዳሉ።+
4 ድሃውን ከመንገድ ያስወጣሉ፤
በዚህ ጊዜ የምድሪቱ ምስኪኖች ከእነሱ ለመሸሸግ ይገደዳሉ።+
5 ድሆች በምድረ በዳ እንዳሉ የዱር አህዮች፣+ ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤
በበረሃ ለልጆቻቸው ምግብ ይፈልጋሉ።
6 ከሌላው ሰው እርሻ እህል* ለመሰብሰብ ይገደዳሉ፤
ከክፉውም ሰው የወይን እርሻ ይቃርማሉ።
7 ያለልብስ ራቁታቸውን ያድራሉ፤+
ብርድ የሚከላከሉበት ልብስ የላቸውም።
8 ከተራሮች በሚወርደው ዝናብ ይበሰብሳሉ፤
መጠለያ ስለማያገኙ ዓለት ያቅፋሉ።
9 አባት የሌለው ልጅ ከእናቱ ጡት ላይ ተነጥቋል፤+
የድሃውም ልብስ በመያዣነት ተወስዷል፤+
10 ያለልብስ ራቁታቸውን ለመሄድ ይገደዳሉ፤
ተርበው እያሉም ነዶ ተሸክመው ይሄዳሉ።
ፊቱንም ይሸፍናል።
16 በጨለማ ቤት ሰብረው* ይገባሉ፤
ቀን ላይ ተሸሽገው ይውላሉ።
ለብርሃን እንግዳ ናቸው።+
17 ለእነሱ ንጋት እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነውና፤
ድቅድቅ ጨለማ የሚያስከትለውን ሽብር ያውቁታል።
18 ይሁንና ውኃ በፍጥነት ጠርጎ ይወስዳቸዋል።*
ርስታቸውም የተረገመ ይሆናል።+
ወደ ወይን እርሻቸው አይመለሱም።
20 እናቱ* ትረሳዋለች፤ ትልም ትመጠምጠዋለች።
ዳግመኛ አይታወስም።+
ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።
21 በመሃኒቱ ላይ ያደባል፤
መበለቲቱንም ይበድላል።
22 አምላክ* ኃይሉን ተጠቅሞ ብርቱ ሰዎችን ያጠፋል፤
ከፍ ከፍ ቢሉም ሕይወታቸው ዋስትና የለውም።
24 ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ከዚያም ደብዛቸው ይጠፋል።+
ዝቅ ዝቅ ይደረጋሉ፤+ ደግሞም እንደ ማንኛውም ሰው ይሰበሰባሉ፤
እንደ እህል ዛላ ይቆረጣሉ።
25 እንግዲህ አሁን እኔን ውሸታም ሊያደርገኝ፣
ወይም ቃሌን ሊያስተባብል የሚችል ማን ነው?”