ኢዮብ
አንዳች ሳላስቀር ብሶቴን አሰማለሁ።
በታላቅ ምሬት* እናገራለሁ!
2 አምላክን እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘በደለኛ ነህ አትበለኝ።
ከእኔ ጋር የምትሟገተው ለምን እንደሆነ ንገረኝ።
4 ዓይንህ የሥጋ ለባሽ ዓይን ነው?
ወይስ የምታየው ሟች የሆነ ሰው በሚያይበት መንገድ ነው?
8 የገዛ እጆችህ ቀረጹኝ፤ ደግሞም ሠሩኝ፤+
አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ልታጠፋኝ ነው።
10 እንደ ወተት አላፈሰስከኝም?
እንደ እርጎስ አላረጋኸኝም?
11 ቆዳና ሥጋ አለበስከኝ፤
በአጥንትና በጅማት አያይዘህ ሠራኸኝ።+
13 ሆኖም እነዚህን ነገሮች በስውር ለማድረግ አሰብክ።*
እነዚህ ነገሮች ከአንተ እንደመጡ አውቃለሁ።
14 ኃጢአት ብሠራ ትመለከተኛለህ፤+
ከበደሌም ነፃ አታደርገኝም።
15 በደለኛ ከሆንኩ ወዮልኝ!
16 ራሴን ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤+
ዳግመኛም በእኔ ላይ ኃይልህን ታሳያለህ።
17 አዳዲስ ምሥክሮችን በእኔ ላይ ታቆማለህ፤
ቁጣህንም በእኔ ላይ ታበዛለህ፤
በመከራ ላይ መከራ ተደራርቦብኛል።
18 ታዲያ ከማህፀን ለምን አወጣኸኝ?+
ምነው የሰው ዓይን ሳያየኝ በሞትኩ ኖሮ!
19 እንዳልተፈጠርኩ በሆንኩ ነበር!
በቀጥታ ከማህፀን ወደ መቃብር በተወሰድኩ ነበር!’