መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በኔሂሎት።* የዳዊት ማህሌት።
5 ይሖዋ ሆይ፣ ቃሌን አዳምጥ፤+
መቃተቴን ልብ በል።
2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣
ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት በትኩረት አዳምጥ።
5 እብሪተኛ ሰው በፊትህ አይቆምም።
8 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ በዙሪያዬ ስላሉ በጽድቅህ ምራኝ፤
ከመንገድህ ላይ እንቅፋቶችን አስወግድልኝ።+
10 አምላክ ግን ይፈርድባቸዋል፤
የገዛ ራሳቸው ዕቅድ ለጥፋት ይዳርጋቸዋል።+
ከበደላቸው ብዛት የተነሳ ይባረሩ፤
በአንተ ላይ ዓምፀዋልና።
11 አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ሐሴት ያደርጋሉ፤+
ምንጊዜም በደስታ እልል ይላሉ።
ሊጎዷቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ትጠብቃቸዋለህ፤
ስምህን የሚወዱም በአንተ ሐሴት ያደርጋሉ።
12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ የሆነውን ሁሉ ትባርካለህና፤
ሞገስህ እንደ ትልቅ ጋሻ ይሆንላቸዋል።+