መኃልየ መኃልይ
1 ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን+ መዝሙር፦*
ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው።+
ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው።
4 ይዘኸኝ ሂድ፤* አብረን እንሩጥ።
ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል!
በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።
ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ።*
አንተን መውደዳቸው* ተገቢ ነው።
6 ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤
ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና።
ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤
የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤
የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም።
በጓደኞችህ መንጎች መካከል
በመሸፈኛ* ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?”
8 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነ
የመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤
የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።”
9 “ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ* ውብ ነሽ።+
10 ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤*
አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል።
11 በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡ
የወርቅ ጌጦች* እንሠራልሻለን።”
13 ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ+ ነው፤
በጡቶቼ መካከል ያድራል።
15 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ።
እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ+ ዓይኖች ናቸው።”
16 “ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ* ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ።+
አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው።
17 የቤታችን* ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣
ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው።