ኤርምያስ
46 ብሔራትን አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+ 2 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውንና የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በካርከሚሽ ድል ያደረገውን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖን ኒካዑን+ ሠራዊት በተመለከተ ለግብፅ+ የተነገረ መልእክት፦
3 “ትንሹንና* ትልቁን ጋሻችሁን አዘጋጁ፤
ለውጊያም ውጡ።
4 እናንተ ፈረሰኞች፣ ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ።
ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ የራስ ቁራችሁንም አድርጉ።
ጦሩን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁንም ልበሱ።
5 ‘እንዲህ ተሸብረው ያየኋቸው ለምንድን ነው?
እያፈገፈጉ ነው፤ ተዋጊዎቻቸው ተፍረክርከዋል።
በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ብለዋል፤ ተዋጊዎቻቸው ወደ ኋላ አልተመለከቱም።
በየቦታው ሽብር ነግሦአል’ ይላል ይሖዋ።
6 ‘ፈጣን የሆኑት መሸሽ አይችሉም፤ ተዋጊዎቹም ማምለጥ አይችሉም።
በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻ
ተሰናክለው ወድቀዋል።’+
7 እንደ አባይ ወንዝ፣
እንደሚናወጥም የወንዝ ውኃ ሆኖ የሚመጣው ይህ ማን ነው?
ከተማዋንና ነዋሪዎቿን አጠፋለሁ’ ይላል።
9 እናንተ ፈረሶች፣ ወደ ላይ ውጡ!
እናንተ ሠረገሎች፣ በፍጥነት ገስግሱ!
10 “ያ ቀን የሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው። ሰይፉ ይበላል፤ ይጠግባልም፤ ደማቸውንም እስኪረካ ድረስ ይጠጣል፤ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ በኤፍራጥስ ወንዝ+ አጠገብ በሚገኘው የሰሜን ምድር መሥዋዕት* አዘጋጅቷልና።
11 ድንግሊቱ የግብፅ ሴት ልጅ ሆይ፣
ወደ ጊልያድ ወጥተሽ በለሳን አምጪ።+
መድኃኒት የምታበዢው እንዲያው በከንቱ ነው፤
ፈውስ አታገኚምና።+
12 ብሔራት በአንቺ ላይ የደረሰውን ውርደት ሰምተዋል፤+
ጩኸትሽም አገር ምድሩን አናውጧል።
ተዋጊ በተዋጊው ይሰናከላልና፤
ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ወድቀዋል።”
13 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የግብፅን ምድር ለመምታት ስለመምጣቱ ይሖዋ ለነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦+
14 “ይህን በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶል+ አውጁት።
እንዲህም በሉ፦ ‘ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ተዘጋጁም፤
ሰይፍ በዙሪያችሁ ያለውን ሁሉ ይበላልና።
15 ኃያላኖቻችሁ ተጠራርገው የጠፉት ለምንድን ነው?
ጸንተው መቆም አልቻሉም፤
ይሖዋ ገፍትሮ ጥሏቸዋልና።
16 ብዙዎቹ ይሰናከላሉ፤ ደግሞም ይወድቃሉ።
እርስ በርሳቸውም “ተነሱ!
ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ
ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ” ይባባላሉ።’
18 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የተጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤
እሱ* በተራሮች መካከል እንዳለው እንደ ታቦርና+
በባሕር አጠገብ እንዳለው እንደ ቀርሜሎስ+ ሆኖ ይመጣል።
19 አንቺ በግብፅ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣
በግዞት ለመሄድ ጓዝሽን አሰናጂ።
20 ግብፅ እንደምታምር ጊደር ናት፤
ሆኖም ከሰሜን ተናዳፊ ዝንቦች ይመጡባታል።
21 በመካከሏ ያሉት ቅጥረኛ ወታደሮችም እንኳ እንደሰቡ ጥጆች ናቸው፤
ይሁንና እነሱም ጭምር ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ሸሽተዋል።
23 በውስጡ ማለፍ የማይቻል ቢመስልም ጫካዋን ይመነጥራሉ’ ይላል ይሖዋ።
‘ቁጥራቸው ከአንበጣ ይበልጥ ይበዛልና፤ ስፍር ቁጥርም የላቸውም።
24 የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትዳረጋለች።
ለሰሜን ሰዎች ትሰጣለች።’+
25 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አሁን ትኩረቴን በኖእ*+ ከተማ ወደሚገኘው ወደ አምዖን፣+ ወደ ፈርዖን፣ ወደ ግብፅ፣ ወደ አማልክቷና+ ወደ ነገሥታቷ፣ አዎ በፈርዖንና በእሱ ወደሚታመኑት ሰዎች ሁሉ አደርጋለሁ።’+
26 “‘ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾርና* ለአገልጋዮቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ ከዚያ በኋላ ግን እንደቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች’ ይላል ይሖዋ።+
27 ‘አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤
እስራኤልም ሆይ፣ አትሸበር።+
አንተን ከሩቅ ቦታ፣
ዘሮችህንም ተማርከው ከተወሰዱበት ምድር አድናለሁና።+
ያዕቆብ ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም ሳይኖር
ተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ ይቀመጣል።+
28 ስለዚህ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ’ ይላል ይሖዋ፤
‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝና።