የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
110 ይሖዋ ጌታዬን
“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ+
በቀኜ ተቀመጥ”+ አለው።
2 ይሖዋ የኃይልህን በትር ከጽዮን ይዘረጋል፤
“በጠላቶችህ መካከል በድል አድራጊነት ግዛ”+ ይላል።
3 ወደ ጦርነት በምትዘምትበት ቀን
ሕዝብህ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።
ከንጋት ማህፀን እንደወጣ ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት በሚያስደንቅ ቅድስና ከጎንህ ይሰለፋል።
4 ይሖዋ “እንደ መልከጼዴቅ፣+
አንተ ለዘላለም ካህን ነህ!” ሲል ምሏል፤+
ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም።
5 ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤+
በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።+
6 በብሔራት ላይ የፍርድ እርምጃ ይወስዳል፤+
ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል።+
ሰፊ የሆነውን አገር የሚገዛውን መሪ ያደቀዋል።
7 እሱ በመንገድ ዳር ካለው ጅረት ይጠጣል።
በመሆኑም ራሱን ቀና ያደርጋል።