መዝሙር
ቢንያማዊው ኩሽ የተናገረውን ቃል በተመለከተ ዳዊት ለይሖዋ ያንጎራጎረው ሙሾ።*
7 አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+
ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም።+
3 አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የሠራሁት አንዳች ጥፋት ካለ፣
አግባብ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሜ ከሆነ፣
4 መልካም ያደረገልኝን ሰው በድዬ ከሆነ፣+
ወይም ያላንዳች ምክንያት ጠላቴን ዘርፌ ከሆነ፣*
5 ጠላት አሳዶ ይያዘኝ፤*
ሕይወቴን መሬት ላይ ይጨፍልቃት፤
ክብሬንም ከአፈር ይደባልቀው። (ሴላ)
7 ብሔራት ይክበቡህ፤
አንተም ከላይ ሆነህ በእነሱ ላይ እርምጃ ትወስዳለህ።
9 እባክህ፣ የክፉ ሰዎች ክፋት እንዲያከትም አድርግ።
10 ቀና ልብ ያላቸውን ሰዎች የሚያድነው+ አምላክ ጋሻዬ ነው።+
13 ገዳይ የሆኑ መሣሪያዎቹን ያሰናዳል፤
የሚንበለበሉ ፍላጻዎቹን ያዘጋጃል።+
14 ክፋትን ያረገዘውን ሰው ተመልከት፤
ችግርን ይፀንሳል፤ ሐሰትንም ይወልዳል።+
15 ጉድጓድ ይምሳል፤ ጥልቅ አድርጎም ይቆፍረዋል፤
ሆኖም በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ራሱ ይወድቃል።+
16 የሚያመጣው ችግር በራሱ ላይ ይመለሳል፤+
የዓመፅ ድርጊቱ በገዛ አናቱ ላይ ይወርዳል።