3 እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችና
የእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ።+
ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም?
2 ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤+ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤+
የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ።+
3 የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤+
ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤
አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤+
በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ።
4 በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤
እሱ ግን አይመልስላቸውም።
ክፉ ድርጊት በመፈጸማቸው፣+
በዚያን ጊዜ ፊቱን ይሰውርባቸዋል።+
5 ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣+
በጥርሳቸው ሲነክሱ+ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣+
አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
6 ‘ሌሊት ይመጣባችኋል፤+ ራእይም አታዩም፤+
ጨለማ ብቻ ይሆንባችኋል፤ ሟርትም አታሟርቱም።
ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤
ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል።+
7 ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤+
ሟርተኞችም ይዋረዳሉ።
ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖር
ሁሉም አፋቸውን ይሸፍናሉ።’”
8 እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግር
በይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣
ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ።
9 ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣+
እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣
የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤+
10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ።+
11 መሪዎቿ በጉቦ ይፈርዳሉ፤+
ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤+
ነቢያቷም በገንዘብ ያሟርታሉ።+
ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም?+
ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም”+
እያሉ በይሖዋ ይመካሉ።
12 ስለዚህ በእናንተ የተነሳ
ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤
ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+
የቤቱም ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ይሆናል።+