ኢዮብ
21 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “የምናገረውን በጥሞና አዳምጡ፤
የምታጽናኑኝ በዚህ ይሁን።
3 በምናገርበት ጊዜ በትዕግሥት አዳምጡኝ፤
ከተናገርኩ በኋላ ልትሳለቁብኝ ትችላላችሁ።+
4 ቅሬታዬ በሰው ላይ ነው?
ቢሆንማ ኖሮ የእኔ* ትዕግሥት አያልቅም ነበር?
5 እዩኝ፤ በመገረምም ተመልከቱኝ፤
እጃችሁን በአፋችሁ ላይ አድርጉ።
6 ስለዚህ ነገር ሳስብ እረበሻለሁ፤
መላ ሰውነቴም ይንቀጠቀጣል።
8 ልጆቻቸው ሁልጊዜ አብረዋቸው ይኖራሉ፤
ዘሮቻቸውንም ያያሉ።
9 ቤታቸው ሰላም የሰፈነበት ነው፤ የሚያሰጋቸውም ነገር የለም፤+
አምላክም በበትሩ አይቀጣቸውም።
10 ኮርማዎቻቸው ዘር ያፈራሉ፤
ላሞቻቸው ይወልዳሉ፤ ደግሞም አይጨነግፉም።
11 ወንዶች ልጆቻቸው እንደ መንጋ በደጅ ይሯሯጣሉ፤
ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ።
14 ይሁንና እውነተኛውን አምላክ እንዲህ ይሉታል፦ ‘አትድረስብን!
መንገዶችህን ማወቅ አንፈልግም።+
15 እናገለግለው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው?+
ከእሱ ጋር መተዋወቃችን ምን ይጠቅመናል?’+
16 ሆኖም ብልጽግናቸው በእነሱ ቁጥጥር ሥር እንዳልሆነ አውቃለሁ።+
17 የክፉዎች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው?+
መዓት የደረሰባቸውስ ስንት ጊዜ ነው?
አምላክ ተቆጥቶ ጥፋት የላከባቸው ስንት ጊዜ ነው?
18 ለመሆኑ በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣
አውሎ ነፋስም እንደሚወስደው እብቅ ሆነው ያውቃሉ?
19 አምላክ አንድ ሰው የሚደርስበትን ቅጣት ለገዛ ልጆቹ ያከማቻል።
ይሁንና ሰውየው ያውቀው ዘንድ አምላክ ብድራቱን ይክፈለው።+
20 የገዛ ዓይኖቹ የሚደርስበትን ጥፋት ይዩ፤
ደግሞም ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ቁጣ ይጠጣ።+
23 አንድ ሰው ሙሉ ብርታት እያለው፣
ተረጋግቶና ያላንዳች ጭንቀት እየኖረ ሳለ ይሞታል፤+
24 ጭኑ በስብ ተሞልቶ፣
አጥንቶቹም ጠንካራ ሆነው* እያለ በሞት ይለያል።
25 ሌላው ሰው ግን አንዳች ጥሩ ነገር ሳይቀምስ፣
በጭንቀት እንደተዋጠ* ይሞታል።
28 እናንተ ‘የተከበረው ሰው ቤት የት አለ?
ክፉው ሰው የኖረበት ድንኳንስ የት አለ?’ ትላላችሁና።+
29 መንገደኞችን አልጠየቃችሁም?
31 ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?
ለሠራውስ ነገር ብድራቱን የሚከፍለው ማን ነው?
32 እሱ ወደ መቃብር ቦታ ሲወሰድ፣
መቃብሩ ጥበቃ ይደረግለታል።
34 ታዲያ ትርጉም የለሽ ማጽናኛ የምትሰጡኝ ለምንድን ነው?+
የምትሰጡት መልስ ሁሉ ማታለያ ነው!”