መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
እኔን ለማጥፋት የሚያሴሩ ተዋርደው ያፈግፍጉ።
5 በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ ይሁኑ፤
የይሖዋ መልአክም ያባርራቸው።+
6 የይሖዋ መልአክ ሲያሳድዳቸው
መንገዳቸው በጨለማ የተዋጠና የሚያዳልጥ ይሁን።
7 ያላንዳች ምክንያት እኔን ለማጥመድ በስውር መረብ ዘርግተዋልና፤
ያላንዳች ምክንያት ጉድጓድ ቆፍረውልኛል።*
9 እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤*
በማዳን ሥራውም እጅግ ደስ ይለኛል።
10 አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይላሉ፦
“ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ምስኪኑን ብርቱ ከሆኑት፣
ምስኪኑንና ድሃውን ከሚዘርፏቸው ሰዎች ትታደጋለህ።”+
13 እኔ ግን እነሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤
ራሴን* በጾም አጎሳቆልኩ፤
ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ በተመለሰ ጊዜ፣*
14 ለጓደኛዬ ወይም ለወንድሜ እንደማደርገው እየተንቆራጠጥኩ አለቀስኩ፤
እናቱ ሞታበት እንደሚያለቅስ ሰው አንገቴን በሐዘን ደፋሁ።
15 እኔ ስደናቀፍ ግን እነሱ ደስ ብሏቸው ተሰበሰቡ፤
አድብተው እኔን ለመምታት ተሰበሰቡ፤
ዘነጣጠሉኝ፤ በነገር መጎንተላቸውንም አልተዉም።
17 ይሖዋ ሆይ፣ ዝም ብለህ የምታየው እስከ መቼ ነው?+
18 ያን ጊዜ በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤+
በብዙ ሕዝብ መካከል አወድስሃለሁ።
20 የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣምና፤
ከዚህ ይልቅ በምድሪቱ በሰላም በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ።+
21 እኔን ለመወንጀል አፋቸውን ይከፍታሉ፤
“እሰይ! እሰይ! ዓይናችን ይህን አየ” ይላሉ።
22 ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል።+
ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+
23 ለእኔ ጥብቅና ለመቆም ንቃ፤ ተነሳም፤
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ተሟገትልኝ።
24 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤+
በእኔ እንዲፈነድቁ አትፍቀድ።
25 በልባቸው “እሰይ! የተመኘነውን አገኘን”* አይበሉ።
ደግሞም “ዋጥነው” አይበሉ።+
26 እኔ ላይ በደረሰው ጉዳት የሚፈነድቁ ሁሉ
ይፈሩ፣ ይዋረዱም።
በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።
27 በእኔ ጽድቅ የሚደሰቱ ግን እልል ይበሉ፤
ሁልጊዜም እንዲህ ይበሉ፦
“በአገልጋዩ ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ ከፍ ከፍ ይበል።”+