ኢዮብ
9 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “እርግጥ ነገሩ እንዲህ መሆኑን አውቃለሁ።
ሆኖም ሟች የሆነ ሰው ከአምላክ ጋር ተሟግቶ እንዴት ትክክል ሊሆን ይችላል?+
4 እሱ ጥበበኛ ልብ አለው፤ ኃይሉም ታላቅ ነው።+
እሱን ተገዳድሮ ከጉዳት ማምለጥ የሚችል ማን ነው?+
5 ማንም ሳያውቅ ተራሮችን ከስፍራቸው ይወስዳል፤*
በቁጣውም ይገለብጣቸዋል።
6 ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤
በመሆኑም ምሰሶዎቿ ይንቀጠቀጣሉ።+
9 የአሽ፣* የከሲልና* የኪማ ኅብረ ከዋክብትን*+
እንዲሁም የደቡቡን ሰማይ ኅብረ ከዋክብት* ሠርቷል፤
10 ታላላቅና የማይመረመሩ ነገሮችን፣
ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ድንቅ ነገሮች ያደርጋል።+
11 በአጠገቤ ያልፋል፤ እኔ ግን ላየው አልችልም፤
አልፎኝ ይሄዳል፤ እኔ ግን አለየውም።
12 አንዳች ነገር ነጥቆ ሲወስድ ማን ሊከለክለው ይችላል?
‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችልስ ማን ነው?+
14 በመሆኑም ለእሱ መልስ ስሰጥ፣
ይልቁንም ከእሱ ጋር ስከራከር አስቤ መናገር ይጠበቅብኛል።
15 ትክክል ብሆን እንኳ መልስ አልሰጠውም።+
ዳኛዬን* ምሕረት ከመለመን ሌላ ምንም ማድረግ አልችልም።
16 ብጠራው ይመልስልኛል?
18 ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አይሰጠኝም፤
መራራ ነገሮችን ያጠግበኛል።
19 የኃይል ጉዳይ ከሆነ እሱ ኃያል ነው።+
የፍትሕ ጉዳይ ከተነሳ ‘ማን ሊጠይቀኝ* ይችላል?’ ይላል።
22 ምንም ለውጥ የለውም። ‘እሱ ንጹሑንም* ሆነ ክፉውን ያጠፋል’
የምለው ለዚህ ነው።
23 ደራሽ ውኃ በድንገት ሰዎችን ቢያጠፋ፣
እሱ ንጹሐን ሰዎች በሚደርስባቸው ሥቃይ ያፌዛል።
ይህን የሚያደርገው እሱ ካልሆነ ታዲያ ማን ነው?
25 ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤+
መልካም ነገር ሳያይ ፈጥኖ ይነጉዳል።
26 ከደንገል እንደተሠሩ ጀልባዎች፣
የሚያድኑትንም ነገር ለመያዝ ወደ ታች እንደሚወረወሩ ንስሮች ይከንፋል።
27 ‘ብሶቴን እረሳለሁ፤
የፊቴን ገጽታ ቀይሬ ደስተኛ እሆናለሁ’ ብል እንኳ፣
28 ከሥቃዬ ሁሉ የተነሳ አሁንም ፍርሃት ይሰማኛል፤+
ንጹሕ ሆኜ እንደማታገኘኝ አውቃለሁ።
29 በደለኛ* ሆኜ መገኘቴ አይቀርም።
ታዲያ ለምን በከንቱ እደክማለሁ?+
32 መልስ እሰጠው ዘንድ፣
ችሎት ፊትም አብረን እንቀርብ ዘንድ እሱ እንደ እኔ ሰው አይደለምና።+